Connect with us

አርቲስት ሳያት ደምሴ ኢቢ ኤስ ላይ ስለ ታገቱት ተማሪዎች…

አርቲስት ሳያት ደምሴ ኢቢ ኤስ ላይ ስለ ታገቱት ተማሪዎች...
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

አርቲስት ሳያት ደምሴ ኢቢ ኤስ ላይ ስለ ታገቱት ተማሪዎች…

“…ቁጭ ብሎ እንደሚወራው አይደለም። ከምናውቀው ካሰብነው ሂደት ውጭ የሆኑ ነገሮች ይኖራሉ። ግን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሴት፣ እህት፣ ጓደኛ፣ቤተሰብ፣ ልትማሪ ወጥተሽ፣ ያውም ያልተማረ ቤተሰብ ሳያምንበት፣ ቤት እንድትሰሪ እየፈለገ፣ የሚያስተዳድረውን ወይንም ኃላፊነት የሰጠውን ሰው ልጆቻችሁን ማስተማር ከዚህ ደረጃ ያደርስላችኋል፣ ልጆቻችሁ ቢማሩ አሁን የምታደርጉትን የእህል አዘራር ፣ መንገዱን ይቀይሩላችኋል፣ ህክምና ያደርጋሉ ተብለው የላኳቸው ቀጥሎ እንደማህበረሰብም የሚያስተምረው አለማስተማርን ነው። እንደ ሴት ደግሞ አቅምን ከማጣት የበለጠ ምንም ጥቃት የለም። ሰው ወደ ጦርነት የሚሄድ ክብሩ ሲነካ ነው።

የተፈጥሮ ነገር ሲሆን ከራስሽ ጋር አልቅሰሽ ትወጭዋለሽ። እግዚያብሔር ያመጣው ነው ብለሽ ትተይዋለሽ። እንደ ወላጅ ግን ከዚህ በላይ አቅም ማጣት ምን አለ? ግድግዳው፣ በሩ ሌላው ልክ ሆኖ ጣራው ሲነሳብሽ ብለሽ አስቢው። በምን ቃል ይገለፃል? እኔ የከፋኝ ነገር፣ ዛሬ ልትሞች ነው ተብሎ መሞት ይሻላል። እየተደረገ ያለው ነገር ልክ አይደለም። እየተደረገ ያለው ነገር እንደሴትም እንደ ሀገርም ልክ አይደለም። ከዚህ የበለጠ ምን ይመጣል? የእውነት ብታስቢው ምን ይመጣል? ብዕርን ይዘሽ ሄደሽ ስለ መሳርያ! እነዚህ ሴቶች ሲመለሱስ ምንድን ነው የሚሆኑት? ምን አይነት እሳቤ ነው የሚኖረው? ከዛ ደግሞ አንድ አካባቢ ብቻ ያለውን ስሜት ይግለፅ ሲባል! እንደዚህ ሆነናል እንዴ? የአንች ህመም ለሆነ ሰው ብቻስ ከሆነ እንዴት ነው እንደ ሀገር የምትቀጥይው? የሕግ የበላይነት አለ ተብሎ እንደሚታሰብ ሀገር፣ የሚጠብቀኝ ሰው አለ፣ ለዚህም ነው ግብር የምከፍለው፣ ለዚህ ነው ባለኝ መንገድ የምሄደው በምትይበት እንደ ቀላል ነገር ሲወራ ወደ ቤት መግባታችንስ በምን እርግጠኛ ነን? ማድረግ የሚገባውን ሁሉ ማድረግ እፈልጋለሁ። እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም። እህቴ ብትሆንስ? እኔ ብሆንስ? ሰው ያልገባው ችግሩ አይደለም። ችግሩን ትደርሽበታለሽ። እነዚህ ሴቶች መቼም አንብበው አይመጡም! አሰልጥነዋቸው አይመጡም። ሲመጡ ምንድን ነው የሚሆነው? እኔ መሄድ ያለብኝ ቦታ ሁሉ ሄጄ የተነገሩኝ መልሶች በጣም የሚያሳፍሩ ስለሆኑ፣ የሚመለከተው አካል ማድረግ የሚገባውን ቢያደርግ እላለሁ። ይህ ለማንም የምታወሪው አይደለም። (የምጠላው ነገር ቲቪ ላይ መጥቶ ማልቀስ ነው።)

ከመንደራቸው ያን ጥለው ሄደው፣ ተጠብቀው ወጥተው፣ ትዳርን ትተው ነው። እኛ ገጠር ላይ ብዙ ፕሮጀክት ሰርተናል። አንዲት ሴት ስትሄድ የአካባቢው ሕዝብ የሚያስበው ቆማ የቀረች ሴት ናት ብሎ ነው። ስለዚህ የከተማው ወንድ ካልሆነ የአካባቢው ወንድ አያገባትም። ይህንን ሁሉ አልፈሽ መጥተሽ፣ በጊዜ ከመዳር አልፈሽ መጥተሽ፣ ልጄ የሆነ ቦታ ደረሰችልኝ (ወላጆቻቸውን አይተሻል።) እኔ እንጃ ……። ሁሉም ሰው ወደራሱ ይመልከትና ሰዎኛ የሆነ መልስ ቢሰጥ። ማድረግም ካለብን ማድረግ ያለብን ነገር ቢነገረን እላለሁ። እውነት የሚመለከተው አካል ካለ የሚያደርገውን ያድርግ።”

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top