Connect with us

ጠቅላይ ሚኒስትሬ ምን ሆነዋል?

ጠቅላይ ሚኒስትሬ ምን ሆነዋል?

ህግና ስርዓት

ጠቅላይ ሚኒስትሬ ምን ሆነዋል?

ጠቅላይ ሚኒስትሬ ምን ሆነዋል?
(ጫሊ በላይነህ)

የደምቢዶሎ ተማሪዎች መታገት ጉዳይ በመንግሥታችን አልተካደም። የጠ/ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው 21 አስለቅቀን 6 ቀርተዋል የሚል የምስራችም፣ መርዶም የሚመስል ነገር ከነገሩን ዛሬ 13 ቀናትን ደፍነዋል። ቃል አቀባዩ ከመንግሥት የተቀበሉትን ወይንም ከአለቆቻቸው በል የተባሉትን መረጃ በመናገራቸው ልወቅሳቸው አልደፍርም። ምክንያቱም የሚናገሩትን ሁሉ ካላየሁኝ፣ ካላረጋገጥኩኝ ሊሉ የሚችሉበት ዕድል ጠባብ እንደሚሆን እገነዘባለሁና። ግን ሲናገሩ ሾላ በድፍን አይነት ነበር። “ተማሪዎቹን ያገተው ማንነው? ለምን አላማ? መንግስት በምን መልኩ ከእነማን ጋር ተደራደረ? ከአሸባሪ ሀይል ጋር መደራደሩስ አግባብነቱ እስከምን ድረስ ነው…” የሚሉ ዝርዝር መረጃዎችን አልነገሩንም። ወይንም ሆን ተብለው ዘለዋቸዋል። ይኸም ሁሉ ሆኖ እስካሁን ልጆቹ ተለቀዋል ከሚለው ወሬ ፈቅ ያለ ነገር አለመገኘቱ ነገሩን አነጋጋሪ አድርጎታል። መንግሥትም በቃለ አቀባዩ በኩል የለቀቀውን መረጃ ተአማኒነት ጥያቄ ላይ ጥሎታል።

የመንግሥትን “ታጋቾች ተለቀዋል” መረጃ ተከትሎ የተጎጂ ወላጆች፣ ቤተሰቦች “ልጆቻችን የታሉ” ማለታቸው ትክክለኛ ጥያቄና የሚጠበቅ ነው። መንግሥትም ልጆቹን እንደተናገረው በሰላም አስለቅቆ ከሆነ ከቤተሰባቸው ጋር እንዲገናኙ ማድረግ ወይንም ይህን ማድረግ የማይችልበት ምክንያት ካለው በወቅቱ ለህዝብ መግለፅ ይገባው ነበር። ከዚህ ይልቅ እየወጡ ያሉት የመንግሥት አካላት የተምታቱ መረጃዎች ይበልጥ ስጋትን፣ ይበልጥ መጠራጠርን የሚዘሩ ናቸው። በልጆቹ ጉዳይ “መረጃ የለንም፣ አናውቅም” ያሉ አካላት በድንገት ተነስተው የተለቀቁት ልጆች ወደዩኒቨርሲቲ ተመልሰዋል ይላሉ። ወላጆች ወደዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ልጆቹን አያገኙም። ሌላኛው ደግሞ ይነሳና መረጃው ለጠ/ሚኒስትሩ ተላልፏል ይላል። ጠ/ሚኒስትሩ ግን መንግስት ባመነው ወደ27 ተማሪዎች የታገቱበትን አብይ ጉዳይ በዝምታ እያስታመሙት ይመስላል።

ጠ/ሚኒስትራችን የካብኔያቸው የፆታ ስብጥር ገሚሱ በሴቶች እንዲያዝ በማድረጋቸው ስመጥር ናቸው። በተሾሙበት ዕለት ስለእናት፣ ስለሴቶች ያላቸውን አክብሮትና ፍቅር በማጋራት የብዙዎችን ቀልብ የሳቡ ናቸው። የህብረተሰቡ ግማሽ አካል እንደሆኑ የሚነገርላቸው ተማሪ እህቶቻችን፣ ልጆቻችን ሲታገቱ፣ ችግር ላይ ሲወድቁ ግን በሁለት መስመር የቲውተር ፖስት እንኳን ማዘናቸውን ለመግለጽ ተቸግረው መታየታቸው ግር ያሰኛል።ምን ሆነው ነው ያስብላል።

ከምንም በላይ ደግሞ እጅግ የማከብራቸውና የእኔ ኘረዝደንት በመሆናቸው የምኮራባቸው ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የቀድሞ የሴቶች መብት ተሟጋችዋ የአሁኑ የጠቅላይ ፍርድቤት ኘረዝደንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ታጋዩ ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ኮሚሽነር ድምፃቸውን ማጥፋት ለሰሚው ግራ ነው። ምን ሆነው ነው የሚያስብል ነው። ምናልባት ሰዎቹ ምንም ባለመናገር ለመንግሥት ያላቸውን ታማኝነት እየገለፁ ይሆን? እንጃ!.. ማን ያውቃል?! በግሌ ግን ምክንያታቸው ምን ሊሆን ይችላል በሚል ለማሰላሰል ሞክሬ የተረፈኝ በከንቱ ጉንጪን ማልፋት ብቻ ነው።
ሲጠቃለል ይኸ የመንግሥታችን ዝምታ መጨረሻው ምን ይሆን? እስቲ ሀሳብ ስጡበት?

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top