Connect with us

በስትሮክ ጉዳት የደረሰበትን ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢን ለማሳከም የድጋፍ ጥሪ ቀረበ።

ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢን ለማሳከም የድጋፍ ጥሪ ቀረበ
Photo: Facebook

ዜና

በስትሮክ ጉዳት የደረሰበትን ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢን ለማሳከም የድጋፍ ጥሪ ቀረበ።

በሥራ ላይ እያለ በድንገት በጭንቅላት ደም መፍሰስ /ስትሮክ/ ጉዳት የደረሰበትን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢ ለተጨማሪ ህክምና የሚውል የድጋፍ ጥሪ ቀረበ፡፡

ታህሳስ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በሥራ ላይ እንዳለ ድንገት ራሱን ስቶ በመውደቁ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት መሆኑን እሱን ለማሳከም የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

የኮሚቴው አባል ጋዜጠኛ ተስፋዬ አባተ ለኢቲቪ እንዳስታወቀው፣ ጋዜጠኛ ስለሺ የጭንቅላት ደም መፍሰሱ ከገጠመው አንስቶ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ችግሩ እንዳይባባስ የሚያስችል ህክምና በማግኘት ላይ ነው፡፡

በተለይም ቀጣይ ህክምና እንዲያገኝ ሀኪሞች በቅድሚያ የደም ግፊቱን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህክምና እያደረጉለት መሆኑን ጋዜጠኛ ተስፋዬ ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛና ተርጓሚ ስለሺ ዳቢ ምንም እንኳን በአገር ውስጥ አቅም በፈቀደ መጠን የህክምና ክትትል እየተደረገለት ቢሆንም፣ በአንድ ወገን ያለው አካሉ የማይንቀሳቀስ በመሆኑ የተሻሉ የሕክምና አማራጮችን በመጠቀም ወደ ቀድሞው ጤንነቱ እንዲመለስ ኮሚቴው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉለት አስተባበሪ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል፡፡

በመሆኑም ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢን ለመርዳት ፍላጎቱ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በባለቤቱ ስም በተከፈተ በኢትዮጵያዊያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000128435337 በኩል ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ሆሊዉድ ሰራሽ ፊልሞችን ወደ አማርኛ በመተርጎምና ለተመልካች እንዲደርሱ አድርጓል፡፡
በኢትዮጵያ ሬድዮ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ኤፍ ኤም 104.7 በእንግሊዝኛ ክፍል በጋዜጠኝነት ብሎም በኃላፊነትም አገልግሏል፡፡

በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የማስተርስ ዲግሪውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናው ጋዜጠኛ ስለሺ ዳቢ፣ትዳር መስርቶ የ5 እና የ 2 ዓመት ወንድ ልጆች አፍርቷል፡፡

ስለሺ ዳቢ ወይም በፊልም ትርጉም ስራው በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፋት በሚያውቁት ስሙ “ትርጉም በስለሺ” እየተባለም ይጠራል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top