Connect with us

ኡስታዝ አህመድን ጀበል ከ ኤል ቲቪ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ከተናገራቸው አስገራሚ ንግግሮች

ኡስታዝ አህመድን ጀበል ከ ኤል ቲቪ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ከተናገራቸው አስገራሚ ንግግሮች
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ኡስታዝ አህመድን ጀበል ከ ኤል ቲቪ ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ከተናገራቸው አስገራሚ ንግግሮች

1.”በዶክተር ጀማል አብዱልቃድር ቦታ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ የተመረጡት ዶክተር ጀማል አብዱልቃድር ሙስሊም በመሆናቸው ሙስሊም የኢትዮጵያ መሪ መሆን አይችልም በሚል ጫና ነበር። ይህንን ዶ/ር ነጋሶ በመፅሃፋቸው አስቀምጠውታል”

2. “ዛሬም ላይ እንኳን ጄኔራል አደም መሐመድ ሙስሊም ስለሆነ ብቻ እንዴት የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ይመረጣል ብለው ተቃውሞ ያቀረቡ ሰዎችም ይሁን አንድ አንድ የመንግስት ባለስልጣናት ነበሩ። ሰው መለካት እና መመዘን ያለበት በብቃቱ እና በክህሎቱ ነው”

3. “አንዲትን ነፍስ ያጠፋ ሰው ሁሉንም ነፍስ እንዳጠፋ ይቆጠራል፤ አንዷን ያዳነ ሁሉንም ነፍስ እንዳዳነ ይቆጠራል። ቁርዓን የሚያስተምረው ይህንን ነው፣ ኢስላምም ይህ ነው”

4. “አንድ የአላህ ነብይ ጉንዳን አስቸገረችው። ከዚያ ጋዝ ለቆ ሁሉንም ጉንዳኖች አቃጠላቸው። አላህ በዚህ ምክንያት ያንን ነብይ ኮነነው። አንዷ ጉንዳን ነች የነከሰችህ ሌሎቹ ምን አጠፉና ነው ንፁሃን ጉንዳኖችን በዚህ መልኩ ያቃጠልከው ብሎ የአላህ ነብይ ተኮነነ ብለው ነብዩ (ሰዐወ) ነግረውናል። ኢስላም እንኳንስ ለሠዎች ነፍስ ይቅርና ንፁሃን ጉንዳኖች ለምን ተገደሉ ብሎ የኮነነ ነው”

5. “ሠላማዊ መሆናችን ማረጋገጥ አይጠበቅብንም ምክንያቱም ሌሎች እምነቶች አረጋግጠው አይደለም የሚኖሩት”

6. “መስጊድን ካቃጠሉት በላይ የሚያሳስበኝ ለምን ተቃወምክ የሚሉት ናቸው። ምክንያቱም አቃጣዮች በስሜት ተነሳስቶ ሊሆን ይችላል ያንን ስናወግዝ ለምን አወገዛችሁ ለምን ተናገራችሁ የሚሉት ግን የባሰ ያሰጋሉ”

7. “እኔ በህይወቴ ሞጣ ሄጄ አላውቅም ዝም ብሎ እዚህ ግባ የማይባል ነገር የሚያወሩት የተፈፀመውን ጥፋት ለማድበስበስ የሚደረግ ጥረት ነው”

8. “ከፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ተወክሎ የሄዱት ሰዎች ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተቃጠለ የተባለውን ለማጣራት ሲሄዱ የተቃጠለው ቤተመቅደስ ውስጥ ስለሆነ እናንተ ደግሞ ሙስሊሞች ስለሆናችሁ ውስጥ መግባት አትችሉም ተብሎ ውጪ ወንበር ላይ እንዳስቀመጧቸው፤ ነገር ግን በግቢው ውስጥም ይሁን በቤተክርስቲያኑ ላይ ምንም ነገር እንዳላዩ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል”

9. “መስጅድ መቃጠሉ ትክክል አይደለም ብዬ ፅፌአለሁ፣ ወደፊትም እቀጥላለሁ። ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ለምን ብየ ፅፌአለሁ። ገፄን ማየት ይቻላል። ደብል ስታንዳርድ ለማንም አያዋጣም። መስጅድ ሲሆን አሸባሪ ምናምን ብሎ መፃፍ አያስኬድም። ዋናው እኔ ትክክል መሆኔን ልመን እንጂ የነሱ ወሬ አያስጨንቀኝም። ደግሞም እንደዚህ የሚያወሩት ሰዎች ምንም አያመጡም”

10. “ይህ አይነት ችግሮች መፍትሄ የሚያገኙት እውነት እውነት መነጋገር ሲጀመር ነው። እውነት እውነት ከተነጋገርን በኋላ ጥፋት ያጠፋውን ሰው ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ነው። ሙስሊሙም ውስጥ እብድ የለም ክሪስቲያኑም ውስጥ እብድ የለም ሁሉም ፍፁም ነው ብለን ማሰብ ጋር ከመጣን በጣም ጥፋት ነው። መስጊድም ይሁን ቤተክርስትያንን የሚያቃጥል ሰው ሀይማኖት አለው፣ ከሌለው/Atheist ከሆነም እምነት አለው፤ የሆነ ነገር አምነዋል። የዛን ሰውዬ እምነት/ሀይማኖት generalize አድርገን ሙስሊሞች ፈፀሙ፣ ክሪስቲያኖች ፈፀሙ ብለን ካጠቃለልን ግን የበለጠ አደገኛ ነገር ነው። የፈፀመው 10 ይሁን 300፣ አንድም ይሁን ያደረገው ሰው ነው የሚጠየቀው እንጂ አብሮ ከጀርባ ካላገዘ፣ ተሳታፊ ካልሆነ፣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሽፋን ካልሰጠ የዛ አካል አድርገን መውሰድ በጣም አደገኛ የሆነ ነገር ነው”

11. “በሶማሌ ክልል ቤተክርስቲያንን ያቃጠሉ ሰዎች ተይዘው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ሌላም ቦታ ያሉ ካሉም በተመሳሳይ ተይዘው መቀጣት አለባቸው። መስጂድም ላይ እንዲሁ በጠቅላላ ተይዘው ሊጠየቁ ይገባል”

12. “እንደነዚህ አይነት ክስተቶች ዝም ተብሎ ሊታዩ አይገባም። አንድ ሲጀመር አንድ ላይ ቆመን ካላስቆምን ይቀጥላል። ከመንግስት አካልም ጠበቅ ያለ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። የእኔ ክልል ነው፣ የእኔ ሰዎች ናቸው እያልን ሽፋን የሚንሰጥ ከሆነ አደገኛ ነው። ከዚያ በዘለለ አስተሳሰቡ ከዬት መጣ ብለን በእስልምናም በክርስትናም መንግስት ጋር ካለውም ምንጩ ምንድነው ይሄን አስተሳሰብ የፈጠረው ብለን ያንን አስተሳሰብ ማከም ያስፈልጋል። እኛ ካድበሰበስን እና ሽፋን ከሰጠነው ቀጥሉ ማለት ነው፤ ነገም ይቀጥላል”

13. “ከምሽቱ 1 ሰዐት ላይ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን፣ ለክልሉ የፀጥታ እና ሰላም ዘርፍ ሃላፊ ለሆኑት አቶ አገኘው ተሻገር ሁኔታውን እንዲያስቆሙ እና ዳንኤል ክብረት በቤተክርስቶያኒቷ በኩል ጥሪ አስተላልፈው እንዲያስቆሙት ደውሎ ነግሯቸው ነበር። የከተማው ልዩ ሃይል ግን ሁሉ ነገር ካበቃ በኃላ ከምሽቱ 3 ሰዐት ነው ቦታው ላይ የደረሰው”

14. “ኢስላም ውስጥ ማንም ይሁን ማን ወንጀል ከሰራ ይቀጣል። እስላም በእራሳችሁም ላይም ቢሆን እውነትን መስክሩ ይላል!”

15. “የእኔ ወገን ፍትህ ነው፣ የእኔ ወገን እውነት ነው!”

16. “ሙስሊም ስላደረገ አብሬው ከቆምኩኝ፣ ክሪስቲያን ስላደረገ በእሱ ላይ ከቆምኩኝ እኔ የቆምኩት ለእውነት ሳይሆን ወገንተኛ ሄኜ ነው ማለት ነው፤ ብሄርም ይሁን ሀይማኖት”

17. “ማንኛውም ሰው በመረጃ ተደግፎ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ከላይ ከሙፍቲው ጀምሮ፣ እኔንም ጨምሮ መቀጣት አለበት፣ በክሪስቲያኑም በኩል እንዲሁ
ከላይ ከፓፓሱ ጀምሮ እስከተርታው አማኝ ጥፋት ከታየበት መቀጣት አለበት፣ ጥፋቱ እንጂ positionኑ/ ደረጃው እና ሀይማኖቱ እዚህ ጋር ለምን ይመጣል? የዛ አይነት ቆራጥነት ያስፈልጋል”

18. “ሙስሊም ሲጠቃ ክሪስቲያኖች ዝም ካሉ ሙስሊሞች ስለሆን ነው ተብሎ ይተሮገማል፣ ክሪስቲያን ሲጠቃ ሙስሉሞች ዝም ካሉ ክርስቲያኖች ስለሆን ነው ተብለው ይወሰዳል። ኦሮሞ ሲጠቃ ሌላው ዝም ካለ ኦሮሞ ስለሆን ነው፣ አማራ ሲጠቃ ሌላው ዝም ካለም አማራ ስለሆን ነው የሚል ትሩጋሜ ይሰጠዋል። ያ አይነት አካሃዶች አጥር እየፈጠረ የበለጠ ወዳልሆነ ደረጃ ሊወስደን ስለሚችል ጉዳዩን የእውነት አጣርቶ እርምጃ ወስዶ መሄድ እንጂ ዝም በሉ፣ አዳፍኑት፣ አታውሩት ማለት አግባብ አይደለም። ይህ የበለጠ ጥፋትን ያመጣል ብዬ ነው የማምነው”

19. “ምርጫ ውስጥ እንደማንኛውም ሰው ልገባም ላልገባም እችላለው። ለአሁኑ ግን አላቀድኩም፣ የጀመርኩት ነገር የለኝም ፕሮግራሜ ውስጥም የለም። ምናልባት አንድ ቀን እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደ ግል ልወዳደር እችላለው”

( Isak Yasin Hasen )

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top