Connect with us

ኢዴፓ ሐገራዊ ለውጡ ከሽፏል አለ

ኢዴፓ ሐገራዊ ለውጡ ከሽፏል አለ
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ኢዴፓ ሐገራዊ ለውጡ ከሽፏል አለ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ምክር ቤት በሃገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልከቶ ጋዜጣዊ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ኢህአዴግ ህዝቡ የሰጠውን ሁለተኛ እድል እንዳልተጠቀመበት ነው ያስታወቀው፡፡

ገዢው ፓርቲ የለውጡ አካል መሆን ሲገባው ራሱ መሪና ባለቤት መሆኑ፤ ኢህአዴግ እኔ አውቅላችኋለሁ ከሚል አስተሳሰቡ እንዳልተላቀቀ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

በህዝብ ጥያቄ መነሻነት የመጣው ለውጥ ፍኖተ ካርታ ያስፈልገዋል ብለን በተደጋጋሚ ሃሳብ ብንሰጥም የሰማን የለም ያለው ኢዴፓ፤ አሁንም በዚህ የለውጥ ጉዞ መዳረሻችን የት እንደሚሆን አይታወቅም ነው ያለው፡፡

ራሱን የለውጥ ሃይል ብሎ የሚጠራው አካል በሃገሪቷ በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን ማስቆምና መቆጣጣር እንዳልቻለም ገልጿል።
በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የስልጣን ሽኩቻና መከፋፈል ሃገሪቷን ወደ አላስፈላጊ መንገድ እየመራት እንደሆነም ተናግሯል፡፡

በመሆኑም ሃገራዊ ምርጫው ከአንድ እስከ ሁለት አመት ሊራዘምና የሽግግር ኮሚሽን ሊቋቋም እንደሚገባ ፓርቲው አሳስቧል፡፡

ኢዴፓ በሃያ አመታት የፖለቲካ ትግል ጉዞው ለሶስተኛ ጊዜ የገጠመውን የህልውና አደጋ በማያዳግም ሁኔታ አክሽፎ ወደ ትግል መመለሱንና በምርጫ ቦርድም ኢዴፓ ቀድሞውንም ቢሆን አለመፍረሱን በሙሉ ድምጽ መቀበሉን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡(ምንጭ:- ኢትዮ ኤፍኤም)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top