Connect with us

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩኘ ምርጫው ካልተራዘመ ችግር እንደሚከተል አስጠነቀቀ

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩኘ ምርጫው ካልተራዘመ ችግር እንደሚከተል አስጠነቀቀ
Photo: Addis Standard

ህግና ስርዓት

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩኘ ምርጫው ካልተራዘመ ችግር እንደሚከተል አስጠነቀቀ

በኢትዮጵያ በቀጣይ ወራት ለማካሄድ የታቀደው 6ኛው ዙር አገር አቀፍ ምርጫ መራዘም እንዳለበት አንድ አለም አቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ።

መቀመጫውን በቤልጂየም ብራሰልስ ያደረገውና በበርካታ ሀገራት የሚከሰቱ ግጭቶችን በማጥናት የመፍትሔ ሀሳቦችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፉ የሀገራት ቀውስ አጥኝ ቡድን /The International Crisis Group/ በመጪው ጊዜያት ኢትዮጵያን ሊያጋጥሟት ከሚችሉ ስጋቶች አኳያ የ2012 ዓ.ም ምርጫ መራዘም እንዳለበት ገልጾ ይህ ካልሆነ ግን የምርጫው መዘዝ አደገኛ እንደሚሆን አስጠንቅቋል፡፡

ድርጅቱ ይህን ይበል እንጂ ከአገሪቱ ህገመንግስት በተቃራኒ ማን በምን ስልጣኑ ምርጫውን እንዲራዘም ሊወስን ይችላል ስለሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ ያለው ነገር የለም።

አለም አቀፍ ተቋሙ ስጋቱን ይግለፅ እንጅ ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ምርጫው ወቅቱን ጠብቆ እንዲካሄድ አስቀድሞ የወሰነ ሲሆን የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ምርጫው በእርግጠኝነት እንደሚካሄድ ሰሞኑን ማሳወቃቸው የሚታወስ ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top