Connect with us

ባንክ የዘረፉት ተቀጡ

ባንክ የዘረፉት ተቀጡ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ባንክ የዘረፉት ተቀጡ

ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የውንብድና ወንጀል የፈፀመው የአቢሲንያ ባንክ ጥበቃ ከግብረ አበሩ ጋር በሁለት ክስ ተከሶ በጽኑ እስራት ተቀጡ::

ተከሳሾች በ1ኛ ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና 671(ለ) ስር የተመለከተዉን በመተላለፈ የማይገባዉን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ 1ኛ ተከሳሽ ገለታው ጎንጥ ወንጀሉን የፈፀመው ቦሌ ቴሌ አካባቢ በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ቅርጫፍ ጥበቃ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ሲሆን ከ2ኛ ተከሳሽ እዩኤል ሰይፉ ከተባለ ጋር በመሆን ስኔ 05 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል የባንኩ ሰራተኞች የዕለቱን ሂሳብ በመዝጋት ላይ ሳሉ 2ኛ ተከሳሽ ቪትስ መኪና 1ኛ ተከሳሽን እና ሌሎች ያልተያዙ ግብረአበሮቹን በመያዝ ወንጀሉ ወደ ተፈፀመበት ቦታ በመምጣት እና ወደ ባንኩ ውስጥ በመግባት በዕለቱ በስራ ላይ የነበሩትን የባንኩን ሰራተኞችን በጩቤና በፌሮ ብረት በማስፈራራት እና የካዝናውን ቁልፍ እንዲከፍቱላቸው በማሳገድ 5,600,896.00 ብር በሁለት ማዳበሪያ ውስጥ በመክተት ይዘውት በነበረው መኪና ላይ ጭነው ከአካባቢው ሊሰወር ሲሉ በፀጥታ ሃይሎች እና በማህበረሰቡ ርብርብ ተይዘዋል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆኑን በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ2ኛ ክስ 1ኛ ተከሳሽ በሕግ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ ሲደረግበት ማንነቱ ደምስ ፋንታዬ በማለት በሃሰተኛ የቀበሌ የነዋሪዎች መታወቂያ በማሳየቱ በፈፀመው ሃሰተኛ ምስክር ወረቀቶች መገልገል ወንጀል ተከሷል፡፡

ተከሳሾች በችሎት ቀርበው ማንነታቸው ተረጋግጦ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን መፈፀማቸውን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማቅረቡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን መርምሮ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሪከርድ ያልቀረበበትና የቤተስብ አስተዳዳሪ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ በማህበራዊ አገልግሎት የሰጠ መሆኑን በቅጣት ማቅለያ በመያዝ 1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ከ6 ወር 2ኛ ተከሳሽ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በማለት ወስኗል፡፡(የፌ/ጠ/ዐ/ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top