Connect with us

ተክለብርሃን አምባዬ በ73 ሚሊየን ብር ግብር ስወራ ተከሰሰ

ተክለብርሃን አምባዬ በ73 ሚሊየን ብር ግብር ስወራ ተከሰሰ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ተክለብርሃን አምባዬ በ73 ሚሊየን ብር ግብር ስወራ ተከሰሰ

የፌዴራል ጠ/ዐ/ሕግ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ድርጅትን በግብር ስወራ በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በስምንተኛ ወንጀል ችሎት ክስ መሰረተ፡፡

በኢትዮጵያ ካሉ የደረጃ አንድ ተቋራጮች መካከል እንዲሁም ከፍተኛ አቅም ካላቸው መካከል አንዱ የሆነው ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ከ2005 አስከ 2008 ባለው ጊዜ ውስጥ መክፈል የነበረበት እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች የተገኘ 70 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የትርፍ ግብር ባለመክፈሉ ክሱ ተመስርቷል፡፡

የንግድ ግብሩ ግዠ ባልተፈጸመባቸው ሐሰተኛ ደረሰኞች በመጠቀም የተሰወረ እንደሆነ እና ደረሰኞቹም የቆረጡት ድርጅቶች በአካል የሌሉ መሆናቸውን ጠቅሶ ነው ዐቃቤ ሕግ ክሱን የመሠረተው፡፡ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ከ25 ሚሊየን አስከ አንድ ሚሊየን ብር የሚደርስ ገቢን ድርጅቱ ሰውሯል ሲል ዐቃቤ ሕግ ክሱን አሰምቷል፡፡፡

በተጨማሪም ከተለያዩ አገልግሎቶች የተሰበሰበ ሶስት ሚሊየን ብር የተጨማሪ እሴት ታክስ በተመሳሳይ ከ2005 አስከ 2008 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ለመንግሥት ሳይከፍል ቀርቷልም ተብሏል፡፡(ምንጭ፡- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top