Connect with us

በድሬደዋ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አማካሪ ምክርቤት ተመሰረተ

በድሬደዋ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አማካሪ ምክርቤት ተመሰረተ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በድሬደዋ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አማካሪ ምክርቤት ተመሰረተ

በድሬደዋ ከተማ የቀበሌ 05 አስተዳደር ፅ/ቤት እና የአዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት አማካሪ ምክር ቤት ምስረታን በትላንትናው ዕለት አካሄደ ፡፡

በምስረታው ላይ የተለያዩ የህብተሰብ ክፍል እና አደረጃጀት ተወካዮች ተገኝተዋል ፡፡

በምስረታ መድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮምሽነር ማኦ ተሾመ ባስተላለፉት መልእክት የአማካሪ ምክር ቤቱ አካበቢውን ሰላም ወደ ቀድሞ ቦታው በመመለስ ረገድ ጉልህ ደርሻ እንዳለው ገለፀው ለዚህም በቅንጅት እና በአብሮነት ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

ሌላኛው በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የቀበሌው ም/ስራ አስፈጻሚና የአማካሪ ምክርቤቱ ሰብሳቢ አቶ አቤል አሸብር ቀድሞ ቀበሌያችን ይታወቅበት ወደ ነበረው ሰላማችን ለመመለስ ሁላችንም በጋራ በመሆን የራሳችን አስተዋፅኦ በማበርከት በከተማ ደረጃ በማህበረስብ አቀፍ ፖሊስ አገልግልት ተጠቃሽ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል ፡፡

በምስረታ መድረኩ ላይ በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ እና አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በመድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽመግሌዎች የሴቶችእና ወጣት አደረጃጀት የትምህርት ቤት ተወካዮች እድሮችን ጨምሮ የጣቢያ እና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተው ምስረታው በድምቀት ተካሂዶ ተጠናቋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top