Connect with us

በሳዑዲ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ሁለት ኢትዮጵያውያን ኤምባሲው ለፍርድ ቤት ይግባኝ አቀረበ

በሳኡዲ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲው አማካኝነት ይግባኝ አቀረቡ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በሳዑዲ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ሁለት ኢትዮጵያውያን ኤምባሲው ለፍርድ ቤት ይግባኝ አቀረበ

– በሌሎች ወንጀሎች የተፈረደባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል፣

ሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሳዑዲ አረቢያ ማረሚያ ቤት ሁለት ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ሰሞኑን የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው መሆኑ እና ጉዳዩ የሚመለከተው የኤምባሲው ባልደረባ የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን ሁለት ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሠዒድ ሙሀመድ እና ያህያ አሊ ጎብኝቶ፣ በጉዳያቸውም ከእነዚሁ ፍርደኛ ዜጎቻችን እና ከማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የኤምባሲው ተወካይ የሞት ፍርድ ከተላለፈባቸው ዜጎች በተጨማሪ የሃያ ዓመት እስራት የተላለፈበትን ሱልጣን ሙሀመድ እና የአራት አመት እስራት ፍርድ የተፈረደበትን ኢብራሂም አሊን መጎብኘቱም ይታወቃል፡፡

ኤምባሲው የተለያየ የፍርድ ውሳኔ የተሰጣቸውን አራት ዜጎች በአካል በማግኘት፣ በማነጋገር እና መረጃዎችን ከመውሰድ እንዲሁም የህግ ባለሙያ/ጠበቃ በማማከር የይግባኝ ጥያቄያቸውን በጽሁፍ እንዲቀርብላቸውና እንዲያዩት በማድረግ በመጨረሻም የእያንዳንዳቸውን የይግባኝ ሰነድ በዛሬው እለት ፍርዱን ላስተላለፈው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ማድረግ ተችሏል፡፡

ከእነዚህ ዜጎች በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የግድያ ወንጀል ተጠርጥረው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው ሁለት ዜጎቻችን ጉዳይ ኤምባሲው በራሱ ወጪ (5000 የሳዑዲ ሪያል) የሞት ፍርድ ውሳኔውን የሚቃወሙበት የይግባኝ ጥያቄ ማቅረቡ እና የጠበቃ ክፍያ በመፈፀም ጠበቃ ቀጥሮ የኢትዮጵያውያኑን ጉዳይ እንዲታይ የሚቻለውን እገዛ እና ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡

እነዚህ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው ዜጎችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ኤምባሲው የሃገሪቱን ህግ በመከተል የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን መፍትሄ እያፈላለገ እና መንግስት ታራሚዎችን በምህረት እንዲለቅ ዲፕሎማሲያዊ ውትወታውን በየጊዜው በሚደረጉ የሥራ ጉብኝቶችና ምክክሮች ወቅት ሲያቀርብ ቆይቷል።

ኤምባሲው ራሱን የቻለ ጉዳይ ፈፃሚዎችን በመመደብ በየወቅቱ ታራሚ ዜጎቻችን ስላለባቸው ችግር፣ ስለተከሰሱበት ሁኔታ፣ ስለፍርድና ተያያዥ ጉዳዮች፣ ፍርድ ጨርሰው በእስር ላይ ስላሉ ዜጎች ሁኔታ፣ አላግባብ ስለታሰሩና ስለተፈረደባቸው፣ የጤና እክል ስለገጠማቸው እና የታራሚዎችን ዝርዝር ጉዳይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሪያድ – ሳዑዲ ዓረቢያ
·

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top