Connect with us

የዩኒቨርሲቲዎቻችን የትናንት ውሎ የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ!
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የዩኒቨርሲቲዎቻችን የትናንት ውሎ የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተ

እንደሚታወቀው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎቻችን በተነሱት ግጭቶች የተለያዩ ጉዳቶች መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ፦
1) በአብዛኛው ዩኒቨርሲቲዎች ከአካባቢው ህብረተሰብ፣ ከዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮችና የአካባቢ አስተዳደር አካላት ጋር በመሆን ተማሪዎችን የማወያየትና የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
.
2) በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ በነበረ ግጭት የማረጋጋት ስራ ላይ በነበሩት የፀጥታ አካላት ጋር በተፈጠረ ግጭትና በተወሰደ እርምጃ ሁለት ተማሪዎች ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡
.
3) ባለፈው ሳምንት በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተከስቶ በነበረ ግጭት ቆስሎ በህክምና ሲረዳ የነበረ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለወላጆች መጽናናትን ይመኛል፡፡
.
የዩኒቨርሲቲዎቻችንን ሠላም ወደ ነበረበት ለመመለስ የሁላችንም የጋራ ጥረት ስለሚጠይቅ ይህንኑን በመገንዘብ መላው የሀገራችን ህዝቦች ሚናችሁን እንድትወጡ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top