Connect with us

ከመኪና ስርቆት ጋር በተያያዘ ስምንት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ከመኪና ስርቆት ጋር በተያያዘ ስምንት ተጠርጣሪዎች ተያዙ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ከመኪና ስርቆት ጋር በተያያዘ ስምንት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በቦሌ ክ/ከተማ አዲስ እየተገነባ ባለው ስቴዲዮም አካባቢ በተለያየ ጊዚያት የመኪናዕቃ እና ከመኪና ውስጥ ዕቃ ሲስርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቁ የምስል ማስረጃዎች አማካኝነት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አዲስ እየተገነባ ባለው ስታዲዮም አካባቢ የመኪና ዕቃ እና ከመኪና ውስጥ ዕቃ ስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦችን የተመለከተ መረጃ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ተለቆ በርካታ ሰዎች ሲቀበቀበሉት የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀውን ቪዲዮ እና ከህብረተሰቡ የደረሰውን መረጃ መነሻ በማድረግ ባደረገው ብርቱ ክትትል የመኪናዕቃ እና ከመኪና ውስጥ ዕቃ ስርቆት የፈፀሙ 8 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሓላፊ ኮማንደር ሰይፈ ሙሉጌታ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባስተላለፈው መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ በሚተላለፉ ጠቃሚ መረጃዎች መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለማጋለጥ ጠቀሜታ እንዳለው ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ከወንጀል ድርጊት ጋር ተያይዞ ማስረጃዎች ያሏቸው ግለሰቦች ሆኑ ተቋማት በየትኛውም አካባቢ ህግን የተላለፈ ተግባር ሲፈጸም መረጃውን ለጸጥታ አካላት በመስጠት የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top