Connect with us

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድና ተያያዥ የአገልግሎቶች ክፍያ ጨመረ

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድና ተያያዥ የአገልግሎቶች ክፍያ ጨመረ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድና ተያያዥ የአገልግሎቶች ክፍያ ጨመረ

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለመስጠትና ተያያዥነት ላላቸው አገልግሎቶች የሚጠየቀው ክፍያ ማሻሻያ ተደርጎበት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 450/2011 ፀድቋል።

በዚህ መሠረት ለአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ 680 ብር፣ ለብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እድሳት፣ ምትክ ወይም ዓለም አቀፍ መንጃ ፍቃድ 620 ብር፣ ለማሰልጠኛ ተቋማት ወይም የራሳቸውን ሰራተኞች ለሚያሠለጥኑ ሌሎች ተቋማት አዲስ ወይም ምትክ ፈቃድ ደግሞ 5 ሺህ 175 ብር ሆኗል።

ከዚህ ባለፈም ለማሰልጠኛ ተቋማት ወይም የራሳቸውን ሰራተኞች ለሚያሠለጥኑ ሌሎች ተቋማት አዲስ ወይም ምትክ ፈቃድ ሲታደስ 2 ሺህ 570 ብር፣ ለቴክኒሽያን አዲስ ወይም ምትክ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ ደግሞ 435 ብር ይሆናል።

እንዲሁም ለቴክኒሽያን ብቃት ማረጋገጫ ለማሳደስ ደግሞ 330 ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡
(ምንጭ:- ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን )

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top