Connect with us

በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ክርስቲያኖች እና አብያተ ክርስቲያን የጥቃት ዒላማ ሆነዋል

በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ክርስቲያኖች እና አብያተ ክርስቲያን የጥቃት ዒላማ ሆነዋል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ ክርስቲያኖች እና አብያተ ክርስቲያን የጥቃት ዒላማ ሆነዋል

በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራ ቅ እና ምዕራብ ሐረጌ የሚገኙ ክርስቲያኖች እና አብያተ ክርስቲያን በአክራሪዎች ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተገለጠ።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሁለት አብያተ ክርስቲያን መቃጠላቸው የተረጋገጠ ሲሆን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችም ለሞት፣ ለስደት፣ ለድብደባ፣ አስገድዶ ሃይማኖት ለማስቀየር መዳረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ኅዳር 2 እና 3 ቀን 2012 ዓ.ም በኩርፋ ጨሌ ረዳ ዋቅጅራ መድኃኔዓለም እና ገልዲድ ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያን መቃጠላቸው የታወቀ ሲሆን በሐረር ዙሪያ ላንጌ ገጠር ከተማ የሚገኘው ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያንም ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በምዕራብ ሐረርጌ መለሳ ወረዳ የሚገኘው የመለሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ አገልጋይ የሆነችው ዕርቀ ሰላም ሞገስ የተባለች ሴት በተፈጸመባት ጥቃት ሕይወቷ ያለፈ ሲሆን የምእመናን ቤታቸው ተቃጥሎ ንብረታቸው መዘረፉን ለማወቅ ተችሏል።

በቀጨ አዲስ ዓለም ቅዱስ ሚካኤል፣ ወጊቻ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሞሌ ቅድስት ማርያም፣ ሳልያ መድኃነዓለም፣ ቆሬ ቅዱስ ገብርኤል በሚገኙ ምእመናን ላይ ድብደባ፣ የንብረት ዘረፋ፣ቤት ቃጠሎ ተፈጽሟል።

ምሥራቅ ሐረርጌ ሜታ ወረዳ የወተር ሕዝበ ክርስቲያን ሊፈጸምበት ከተቃጣ ጥቃት ለማምለጥ በኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልሎ የሚገኝ ሲሆን በሐረር ዙሪያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ምእመናን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተጠግተው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በቀርሳ ወረዳ ደርመሼክ ቀበሌ ቍጥራቸው በውል ያልታወቁ ክርስቲያኖች መስጊድ ውስጥ ተዘግቶባቸው “ካልሰለማችሁ አትወጡም” በማለት እየዛቱባቸው መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።(ምንጭ፡-ማኀበረ ቅዱሳን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top