Connect with us

በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች በስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሕዳር 1 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ምሽት 2፡00 አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት እንዳለፈ ተማሪዎች ተናግረዋል፤ በግጭቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተማሪዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰም ተሰምቷል፡፡

ለአብመድ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች እንደገለፁት ሦስት ተማሪዎች ተጠልፈው ተወስደው የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ሕይወቱ ያለፈው ተማሪ ምንም ዓይነት የሕክምና እርዳታ ሳያገኝ በግቢው ውስጥ ሕይወቱ ማለፉንም ተናግረዋል፡፡ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም ‹‹በተማሪዎች ክሊኒክ ውስጥ ሕክምና ቢያገኙም ለተሻለ ሕክምና ወደ ሆስፒታል አልተወሰዱም›› ብለዋል፡፡ አሁንም አፋጣኝ የሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች መኖራቸውን ነው አስተያዬት የሰጡን ተማሪዎች ያመለከቱት፡፡

‹‹ዛሬም የፀጥታ ስጋት አለብን›› ያሉት ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ግጭቱ መፈጠሩና ሕይወት ማለፉ ይበልጥ ስጋት እንደተፈጠረባቸውም ገልጸዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ መሪዎችና እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ቢያደርጉም መግባባት ላይ አለመደረሱንም ተማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡
ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ኃይሉን አጠናክሮ አስተማማኝ ሠላም እና ደኅንነት እስኪኖር ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመሄድ ቢጠይቁም ዩኒቨርሲቲው ከግቢ እንዳይወጡ እና መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ትዕዛዝ መስጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲው ማብራሪያ እንዲሰጡን ወደ ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ስልክ ብንደውልም አያነሱም፡፡ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እንደሆኑ በተማሪዎች ወደተነገሩን አንድ የሥራ ኃላፊ ደውለን ስለጉዳዩ ብንጠይቃቸውም ግጭት መፈጠሩን እንደሰሙ እና ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዳልሄዱ ነግረውናል፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት ስልክ ሊሰጡን ከተስማማን በኋላ በተደጋጋሚ ስንደውልላቸው ግን የግል ስልካቸው ተዘግቷል፡፡

ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ስናደርግ ብንውልም አልተሳካልንም። ቀን ላይ ከስብሰባ ውስጥ እንደሆኑ በሚያመላክት ድምጽ ሚንስትር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ “ትንሽ ጠብቁኝ” ቢሉንም ከዚያ በኋላ ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም።

አብመድ ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲም ሆነ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር መረጃ እንዳገኘ ያቀርባል፤ መረጃ ለማግኘትም ጥረቱን ይቀጥላል።

(ምንጭ:-አማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top