Connect with us

የእኛ እና የእነርሱ ጉዳይ ….

የእኛ እና የእነርሱ ጉዳይ ....
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የእኛ እና የእነርሱ ጉዳይ ….

የእኛ እና የእነርሱ ጉዳይ ….
(ታምሩ ገዳ)

ምንም እንኳን እንደ አገሩ፣፣ ባህሉ እና ጊዜው ቢለያይም የችግር እና የሀዘን ትልቅ እና ትንሽ የለውም፣ ችግር ያው ከእነስሙ ችግር ነውና። ሰሞኑን የአለም መገናኛ ብዙሀናት ትኩረትን ከሳቡት አሳዛኝ ክስተቶች ውስጥ በፌስ ቡክ የክተት ጥሪ ዘመቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰማኒያ በላይ ሰላማዉ ዜጎች በጎሳ እና ሀይማኖት ተኮር ህይወታቸውን ያጡበት፣ ለአካለ ስንኩልነት እና ከቤት ንብረት የመፈናቀል የተዳረጉበት፣በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት በሰደድ እሳት አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ ከቤት ንብረታቸው በእኩል ሌሊት የተሰደዱበት ሁናቴ ተጠቃሾች ናቸው።

የእኛ አገር ሰሞነኛ ክስተቶችን መለስ ብለን ስንቃኘው ለዘመናት በመከባበር እና በመተማመን የኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በዘራቸው እና በሀይማኖታቸው ብቻ በጠራራ ጸሐይ እና በድቅድቅ ጨለማ ምንም የማያውቁ ህጻናት እና ሴቶች ሳይቀር እጅግ አሳቃቂ በሆነ ሁኔታ የመጨፍጨፋቸው፣ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ዋጋ አጥቶ በምስኪኖች አስክሬኖች ላይ “ፉከራ እና ጉሮ ወሸባዬ” ሲፎከር የተመለከቱ የሀይማኖት አባቶች፣የፖለቲካ መሪዎችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያኖች ልባቸው እና ቅስማቸው በእጅጉ ተሰብሯል።አረ የፈጣሪ፣የህግ እና የመንግስት ያለህ !!!ሲሉም ጩኸታቸውን አሰምተዋል ።

በኢኮኖሚው በአለም አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት ሰሞኑን “ዲያብሎ/ዲያብሎስ ” በተሰኘ በሰዓት ሰማኒይ ማይልስ በሚገሰግስ ንፋስ አማካኝነት የተቀስቀስው የዱር እሳት ከአንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቤታቸው ፣ንብረታቸውን ለቀው ተሰደዋል፣ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አንድ ዘመናዊ ማህበረሰብ ሊያገኛቸው የሚገባው እንደ መብራት ፣ ያለ አውራ ጎዳና ፣ያለ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣ያለ መረጃ አገልግሎት ለቀናት እንዲኖሩ ተገደዋል።

ምንም እንኳን በ ከባቢ የአየር ሙቀት መጨመር የማያምኑት ፕ/ት ዶናል ትራምፕ ዲሞክራቶች ለሚመሯት ለካሊፎርኒያ ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ መርጃ ከፌደራል መንግስቱ ካዝና እንደማይሰጡ ደጋግመው ቢገልጹም በሰሞኑ ቃጠሎ የተገጎዱ ወገኖች በበኩላቸው በሚሊዮኖች ዶላር የሚያወጡ ቤት ንብረቶቻችውን ጥለው በመሄዳቸው ብዙም ሳይቆጩ በምትከ ከሚንቀለቀለው እሳት ውስጥ ለሰአታት በቆይ በብርቱ ትግል እና በተአምር ነጻ ያደረጓቸው ውሾቻቸው፣ድመቶች፣ፍየሎች እና ፈረሶችን ሲመለከቱ ከፍተኛ የመንፈስ እርካታ እንደተሰማቸው ሲናገሩ ተስተውለዋል።አንዳንዶቹም ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በጣም የሚወዷቸው የቤት እንሰሶቻቸውን ማዳን ሳይችል በእሳቱ ተቃጥለው መሞታቸውን ሲረዱ ልክ የቤተሰብ አባላቸው እንደሞተባቸው አድርገው ሲቆዝሙ ተስተውለዋል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top