Connect with us

ቦዪንግ አመነ፤ ይቅርታ ጠየቀ

ቦዪንግ አመነ፤ ይቅርታ ጠየቀ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ቦዪንግ አመነ፤ ይቅርታ ጠየቀ

737 ማክስ ጄቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አምኗል።

የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ምዩለንበርግ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ትናንትና ትናንት ሲጠየቁ ስሕተትና ጥፋት መፈፀሙን አምነው “እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ” ብለዋል።

የኩባንያቸው መታመን እንደገና እንዲያንሠራራ ለማድረግ በርትተው እንደሚሠሩና እንዲያ ዓይነት ጥፋት እንደማይደገምም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የንግድ፣ የሣይንስና የትራንስፖርት ኮሚቴ ተናግረዋል።

የተጎጂዎች ቤተሰቦችና የሕግ ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል።

የቦዪንግ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ትናንት በተወካዮች ምክር ቤቱ የትራንስፖርት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል ሲል የዘገበው VOA ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top