Connect with us

የአዳማ ከተማ የዛሬው ሰልፍ ሰዎችን ለሞት ዳረገ

የአዳማ ከተማ የዛሬው ሰልፍ ሰዎችን ለሞት ዳረገ

ህግና ስርዓት

የአዳማ ከተማ የዛሬው ሰልፍ ሰዎችን ለሞት ዳረገ

አዳማ፤ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።

በአዳማ ከተማ ጠዋት በግምት 2:00 ሰአት ገደማ ጀዋር መሐመድን በመደገፍ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን ረፋዱ ላይ በሰልፈኞቹ የተበሳጩ ወጣቶች ወደጎዳና በመውጣታቸው ግጭት መፈጠሩን የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በግጭቱ የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን የአይን እማኞቹ ለድሬቲዩብ የገለፁ ሲሆን የደረሰው ጉዳት መጠን አልታወቀም።
አንዳንድ ወጣቶች ግርግሩን በመጠቀም ዘረፋ ማካሄዳቸው ታውቋል።

በአሁን ሰአት መከላከያ የገባ ሲሆን ሰልፈኛው በመበተኑ ከተማዋ ወደቀድሞ መረጋጋትዋ ተመልሳለች።

አዲስ አበባ

የአክቲቪስት ጀዋር ደጋፊዎች መኖሪያውን ከበው ዋሉ

የኦሮሞ አክቲቪስት እና የኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ የጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ከትናንት ሌሊት አንስቶ እስከ ዛሬ ከእኩለ ቀነ በኋላ ድረስ በወጣት ደጋፊዎቹ ተከቦ ዋለ።

የአዲስ አበባው DW ዘጋቢ እንደተመለከተው አዲስ አበባ ቦሌ ጃፓን ኤምባሲ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ከሚገኘው ከቤቱ አጥር ውጭ የተገኘው በሺህዎች የሚቆጠር ወጣት «ዐቢይ ይውደም» «ነፍጠኛ ይውደም» የሚሉ መፈክሮችን እያሰማ ተቃውሞውን ሲገልጽ ነበር።

ወጣቶቹ ወደ ጀዋር መኖሪያ አካባቢ መሄድ የጀመሩት « በመኖሪያ አካባቢው በርካታ የመንግሥት ታጣቂዎች እየተሰማሩ እንደሆነ» ጀዋር ትናንት ሌሊት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መልዕክት ካስተላለፈ በኋላ እንደነበር ተዘግቧል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ጀዋር ያስተላለፈው መልዕክት ስህተት ነው የሚል መግለጫ ከሰጡ በኋላ ግን በአካባቢው ተሰብስቦ የነበረው ወጣት ቁጥር ቀስ በቀስ እየቀነሰ መሄዱን ዘጋቢያችን ተመልክቷል።

የDW ዘጋቢ እንዳለው በአካባቢው የነበሩ ባንኮች እና ትምሕርት ቤቶች እንዲሁም ሱቆች ,ዘግተው ነበር። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡት ወቅት ችግር በመፍጠር የኮነኗቸውን የውጭ ዜግነት ያላቸውን የመገናኛ ብዙሀን ባለቤቶች አስጠንቅቀው ነበር። የአሜሪካን ፓስፖርት እንዳለው የተነገረው የጃዋር ጠባቂዎች፣ ትናንት ሌሊት በኃይል ከአካባቢው እንዲለቁ በጸጥታ አስከባሪዎች ሲገደዱ ማየታቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top