Connect with us

ገቢዎች ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አደረገ

ገቢዎች ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አደረገ
Photo: Facebook

ማህበራዊ

ገቢዎች ለሠራተኞቹ የደመወዝ ጭማሪ አደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ማበረታቻ ይሆን ዘንድ ከሃምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የአንድ እርከን ደሞዝ ጭማሪ አደረገ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመስሪያ ቤቱ አስተዳደር ደንብ 155 መሰረት ነዉ ትናንት ባደረገዉ ምክክር የደሞዝ እርከን ጭማሪዉን ያደረገዉ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በልዩ የደሞዝ እስኬል የሚተዳደር በመሆኑ ምክንያት መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ያደረገዉ የደሞዝ ማስተካከያ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽንን ያካላካተተ ነበር፡፡

የደሞዝ ጭማሪዉ ለመስሪያ ቤቱ ከተያዘዉ በጀት የሚሸፈን ይሆናልም ተብሏል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤም መላዉ ሰራተኛ በቅንነትና በትጋት ይበልጥ በማገልገል የ2012 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን እቅድን ለማሳካት መስራት አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ በፓርላማ አድናቆት ማትረፉ የሚታወስ ነዉ::

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top