Connect with us

ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ፓለቲካ

ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የዓለም የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን በማስመልከት የሰላም ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የእውቅና መድረክ የፊታችን እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናወነው ይህ የደስታ መግለጫ ዝግጅት እሁድ ጥቅምት 9፣2012 ዓ.ም ከቀኑ 11 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት እንደሚዘልቅ የሰላም ሚኒስቴር መግለጫ አስታውቋል ሲል ዋልታ ዘግቧል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የ2012 ኖቤል ሰላም ሎሬት ተሸላሚ መሆናቸው ይታወሳል፡፡(ኢኘድ)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top