Connect with us

በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡

አፋር ክልል
Image: ከአፋር ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት

ማህበራዊ

በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡

አልሸባብ የሚፈጸም ጥቃት እንዲቆምና የፌዴራል መንግሥት ሉዓላዊነትን እንዲያስከብር

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከአፋር ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክትው በአፋር ክልል የተለያዩ ከተሞች ሠላማዊ ሠልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡ ሠመራንና አዋሽ ሰባት ኪሎን ጨምሮ ከሠሞኑ ሰልፍ ባልተካሄደባቸው ከተሞች ሕዝቡ ዛሬ ወደ አደባባይ መውጣቱ ነው የተገለጸው፡፡

ሠልፈኞቹ የአፋር ክልል ላይ በውጭ ኃይሎች በተለይም አልሸባብ የሚፈጸም ጥቃት እንዲቆምና የፌዴራል መንግሥት ሉዓላዊነትን እንዲያስከብር መጠየቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአፋር ክልል ከሰሞኑ በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች በተለይም ሴቶችና ሕጻናት ሕይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉም መኖራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት

Source: አብመድ

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top