Connect with us

ወልዲያ ከተማ ለመቀሌ የጻፈችው ደብዳቤ

ወልዲያ ከተማ ለመቀሌ የጻፈችው ደብዳቤ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ወልዲያ ከተማ ለመቀሌ የጻፈችው ደብዳቤ

ወልዲያ ከተማ ለመቀሌ የጻፈችው ደብዳቤ

(አሳዬ ደርቤ ~ ለድሬ ቲዩብ)

ውድ መቀሌ እንዴት ነሽልኝ? ደብረ ጽዮንስ ያለበት ሁኔታ ምን ይመስላል? በጓንት የተሸፈነ እጁን ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው ወይ? ያ ጌታቸው ረዳ’ስ ‹‹ጂን መጠጣት ከድሮን ጥቃት ያድናል›› እያለ አልኮል መጋፈፉን አልተወም ወይ?

እኔ እምልሽ መቅዬ፡- ከጓዳዬ እየተዛቀ ሲላክልሽ የከረመው ዱቄት የዓለም የምግብ ድርጅት ከሚልክልሽ ጋር ሲደመር ስንት ኩንታል ሆነልሽ? ከእነ ማቡኪያው እየተዘረፈ ሲላክ የነበረው ሊጥ’ስ እንጀራው እሚያምር ሆነ ወይ?  የእኛ አካባቢ ጤፍ እንደ ጌታቸው ረዳ ሆድ ውሃ ስለማያነሳ አብሲቱን ስትጥይ እንደ ደጺ እግር ቀጠን አድርጊው፡፡

መቅዬ፡- ከምድርሽ ተነስቶ የወረረኝ መንጋ ሲፈጽምብኝ የከረመውን ግፍ አትጠይቂኝ፡፡ አዲስ ዓመት ለማክበር ስዘገጃጅ ለሃያ ሰባት ዓመት እንደ አገር ሲግጠኝ የኖረው አሮጌ ሥርዓት ተቆጣጥሮኝ በደቦ ስገደል፣ በቡድን ስደፈርና በጅምላ ስቀበር ከረምኩልሽ፡፡ በእነ ተክላይና ምግበይ በሚባሉ የሽብር ቡድን መሪዎች ወልድያ የሚለው ሥሜ ወደ ‹‹ወልዳይ›› ተቀይሮ ተቋማቴ ሲዘረፉ፣ ልጆቼ ሲጨፈጨፉ ሰነበቱ፡፡

በቅርቡ ታዲያ ጀግና ልጆቼ ባደረጉት ተጋድሎ ከጠላቴ መዳፍ ተላቅቄ ከእናቴ እቅፍ መግባት ብችልም ጓዳዬን ሞሰቤ በመራቆቱ የተነሳ የምበላው ቸግሮኛል፡፡ ስለሆነም ከሰሞኑን ወዳንቺ ዘንድ መጥቼ ጤፍና ዱቄት መበደሬ አልቀረም፡፡ክክክክክ

ስቀልድ ነው መቀሌዋ! ወደ ቀየሽ መምጣቴ እርግጥ ቢሆንም ዘራፊውን እንጂ የተዘረፍኩትን ስለማልጠይቅሽ አትጨነቂ! የእራሴን ስንቅ ሸክፌ ነው የምመጣው፡፡ ከዚህ ባለፈም ልጆችሽ ያደረጉብኝን እጅግ ዘግናኝ አረመኔያዊ ድርጊት የእኔ ልጆች ስለማይደግሙት ወንጀለኞችን አሳልፈሽ መስጠት እንጂ ተመሳሳይ ጥቃት ይደርስብኛል ብለሽ እንዳትሸበሪ፡፡

ምክንያቱም ከምድርሽ የተነሱት ወራሪዎች የአማራ እና የአፋር የሚባል ቤተ-እምነት ፈጥረው ደብሩንና መስጊዱን ሲያወድሙ ቢከርሙም የእኔ ልጆች ግን የፈጣሪ ቤተ- እምነትን እና የአሸባሪ ቤተ-መንግሥትን ለይተው የሚያውቁ በመሆናቸው የሚሳለሙትና የሚሰግዱበት እንጂ የሚያወድሙት ቤተ-እምነት አይኖርም፡፡ 

እኅቶቻቸው በደቦ ሲደፈሩ ቢከርሙም የአስገድዶ ደፋሪን ብልት ጨምድደው ለሕግ ከማቅረብ ባለፈ ተመሳሳዩን ለማድረግ የሚፈቅድ ስብዕና የላቸውም፡፡ የእራሳቸውን ስንቅ ይዘው ከመምጣት ባለፈም የተዘረፈ ዱቄትና ሊጥ የሚሸከም ትከሻ የላቸውም፡፡

ከዚህ ውጭ ግን መቀሌዋ የተዘረፉ ተሸከርካሪዎቼን፣ የሕክምና መሳሪያዎቼን፣ ቅርሶቼንና ዋና ዋና ንብረቶቼን መጠየቄ ስለማይቀር ከዘራፊዎቹ ጋር የተዘረፈውን አዘጋጅተሸ ልትጠብቂኝ ይገባል፡፡ እንደ ወትሮው እኅታማች ባንሆን እንኳን ጠላታሞች ሆነን መቅረት ስለሌለብን የተለመደውን ባሕሪሽን አስተካክለሽ ለሕግ ማስከበር ዘመቻው ተባባሪ መሆን አለብሽ፡፡

ከእንግዲህ ህውሓት የተባለ አረማዊ ቡድን ኢትዮጵያን ሊያስተዳድርም ሆነ ከመንግሥት ጋር ሊደራደር ቀርቶ አንቺን መደበቂያው አድርጎ መኖር አይችልም፡፡ በመሆኑም ያ ጌታቸው ረዳ የተባለ ቀልማዳ ሽጉጥ የሚጠጣበት ወኔ ባይኖረው እንኳን በመጠጥ እራሱን ሳያጠፋ በፊት ከእነ ሕይወቱ ልታስረክቢው ይገባል፡፡ ሌሎቹንም እንዲሁ….

ሌላው ደግሞ መቀሌዋ ከአንቺ ምድር እየተመረተ እኔንም ሆነ ኢትዮጵያን ሲያሰቃይ የኖረው ማለቂያ የለሽ ደዌና ሕመም ከእንግዲህ መቆም ይኖርበታል፡፡ አንቺን ከችግርና ከርሐብ የሚታደግ እሕል ጭኖ በመጣ ተሸከርካሪ ርሐብን የሚያስፋፋና ሕይወትን የሚጠፋ መንጋ እያጓጓዙ በአገር ላይ መጫወት ይበቃል፡፡ ከአንድ ክልል በሚመነጭ ችግር በድህነትና በጥይት ሲንገበገቡ መኖር መላው ኢትዮጵያዊ እንደሰለቸው ተረድተሸ ወደ ትክክለኛው መስመር መግባት ይኖርብሻል፡፡

 

‹‹ኤሌክትሪክ ይለቀቀልኝ›› የሚል የመብት ጥያቄሽን ከማቅረብሽ በፊት ጨለማን የሚያከፋፍሉ ወንጀለኞችሽን እጃቸውን አስረሽ ለኢትዮጵያ ሠራዊት ማስረከብ ግድ ይልሻል፡፡ ‹‹የአልሚ ምግብ›› ጥያቄ ከማቅረብ አስቀድሞም ፈርጥጦ የመጣው አውዳሚ መንጋ ትጥቁን ፈትቶ ይቅርታውንና ስንዴውን እንዲጠይቅ ማድረግ ይገባሻል፡፡ 

‹‹ኢንተርኔት ይለቀቅልኝ›› ወይንም ደግሞ ‹‹መንገድ ይከፈትልኝ›› ከማለትሽ በፊትም በሐሰት አካውንት ውስጥ ተደብቆ የማንነትና የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ የሚታትረውን የዲጂታል ወመኔ ቡድን ‹‹በቃህ›› ማለት ይጠበቅብሻል፡፡

ይሄንን ካደረግሽ በኋላም፣ ከህውሓት ካድሬዎችና እሳቤዎች የጸዳ መድረክ አዘጋጅተሽ ‹‹እኔ ማን ነኝ? ፍላጎቴና ምርጫየስ ሀገረ ትግራይን መቀለስ ወይስ ኢትዮጵያን ማፍረስ? ›› በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ተወያይተሸ የሆነ ውሳኔ ላይ እንዲትደርሽ እመክርሻለሁ፡፡ እናት ኢትዮጵያንም ይቅርታ የምትጠይቂበት ድፍረት ፕሮግራም ብታዘጋጅ ጥሩ ነው እልሻለሁ፡፡

በተረፈ ኢትዮጵያን ከፍርሰት፣ እኔን ከባርነት ነጻ ያወጣው ሠራዊት ከሰሞኑን ወዳንቺ ዘንድ መምጣቱ ስለማይቀር የዚህን ሃላፊነት የሚሰማው ሠራዊት ሥም በማጥፋት ፈንታ ከሰው እስከ እንስሳ ያለውን ፍጥረት ሲረሽን፣ የድሃን መኖሪያ ቤት ጨምሮ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት እስከ ቤት እምነት ያሉትን ተቋማት ሲመዘብር እንዲሁም ንጹሐንን ሲደፍርና በጅምላ ሲቀብር የከረመውን አረማዊ ቡድን ያለምንም መንገታገት ከጉያሽ መንጭቀሽ ማስረከብ ይኖርብሻል›› እያልኩ ደብዳቤየን እቋጫለሁ፡፡

ወልዲያ!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top