Connect with us

የግብጽ ”ሥውር ኃይሎች ዘመቻ ” በጨረፍታ…

Social media

ነፃ ሃሳብ

የግብጽ ”ሥውር ኃይሎች ዘመቻ ” በጨረፍታ…

የግብጽ ”ሥውር ኃይሎች ዘመቻ ” በጨረፍታ…(እስክንድር ከበደ ~ ለድሬቲዩብ)

በኢትዮጵያ የሚገኙ ግብጻውያን ባለሀብቶችን በትግራይ ክልል ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ፤ የደረሰባቸውን ኪሳራ ኢትዮጵያ እንድትከፍል ለመክሰስ ውጥን እንዳላቸው የአረብ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር፡፡

የግብጽ ባለሀብቶች ካሳ እንዲከፈላቸው የጠየቁት በመቀሌ የኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረት ሂደቱ በማቋረጡ ለኪሳራ ተዳርገናል በሚል ነው፡፡ በመጀመሪያ 2 ሚሊየን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ኪሳራ ደርሶብናል ሲል ነበር፡፡ ቀስ በቀስ ወደ 10 ሚሊየን ዶላር አድርሰውታል፡፡ የግብጽ ባለሀብቶች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከመቼ ወዲህ እንደገቡና በምን ምርት ላይ እንደተሰማሩ ዘገባዎቹ አይጠቅሱም፡፡

በሚድል ኢስትና በኢጂፕት ቱደይ እንዲሁም በሌሎች የአረብ መገናኛ ብዙሀን ይህንን አስመልክተው የቀረቡ ዘገባዎች አበክረው የሚኮንኑት የኢትዮጵያን መንግስት ሲሆን ፤ የዘገባዎቹ አብዛኛው ይዘት የሚያተኩረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውዝግብና ውጥረት ነው፡፡ ግብጽ በአረብና በአፍሪካ ሀገራት የኢንቨስትመንት ተሳትፎዋ ንጹህ የንግድ ግንኙነት እንዳልሆነ የግብጽ የስለላና ደህንነት ተቋም ታሪክ ይነግረናል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት የምትታወቀው ቻይና ናት፡፡

ቻይና የገነባችውን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስለመግባታቸውም ሆነ ምን ያመርቱ እንደነበር አይታወቅም፡፡ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 70 ግብጻውያን በመቀሌ በኩል ወደ ወደ ኩዌት እንሄዳለን ብለው መንግስት እነዚህን የግብጽ ዜጎች ከጉዞ እንዳናጠባቸው ብልጭ ብላ የጠፋች መረጃ ነበረች፡፡

ኤርትራም የግብጽ ጠላቂ ጀልባዎችና ”አሳ አጥማጆች ” ይዛ በኋላ መልቀቋ ይታወሳል፡፡ በዛው ሰሞን ግብጽና ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በጦር ጄቶችና በሂሊኮፕተሮች የታገዙ የጋራ ልምምዶች ሲያደርጉ መቆየታቸው አይረሳም፡፡

የግብጽ እ.ኤ.አ በ1952 የግብጽ አብዮት ተከትሎ ነበር፡፡ ኤጀንሲው ከወታደራዊ የስለላና ቅኝት አገልግሎት ቢሮ ጋር በአንድነት በዓለም ላይ ንቁ ከሚባሉት የስለላና መረጃ ተቋማት በ5ኛ ደረጃ የሚታይ ነው፡፡ የግብጽ ጄነራል የስለላና ደህንነት ዳይሬክቶሬት በቀድሞ ፕሬዚዳንት ጋማል አብዱ ናስር ነበር፡፡

ዳይሬክቶሬቱ እ.ኤ.አ በ1954 ዓ.ም ለመቋቋሙ ገፊ ምክንያት የሚጠቀሰው ከውጭ ኃይሎች እንደ ብሪታኒያና እስራኤል አሉታዊ ተጽኖዎች እያደረጉ በመምጣታቸው ነበር፡፡ ይህንን የውጭ የስለላና ደህንነት ተቋማት የስለላ ተግባራት ላይ አጸፋ ስለላ የማድረግ ተልኮን ደርቦ እንዲሰራ ተደርጓ፡፡በናስር ክትትልና ቁጥጥር ስር በመሆን ፤የራሱ ህንጻ እንዲኖረው ብሎም የሬዲዮ ፣ የኮምፒተር፣ የፎርጀሪ እና ”ብላክ ኦፕሬሽንስ” Black Operations. በሚል የተለያዩ መምሪያዎች አደራጅቷል፡፡

የግብጽ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጋማል አብደል ናስር የግብጽ የስለላና ደህንነት ተቋም ለሚያከናውናቸው ኦፕሬሽኖች ወጪ የሚሸፍን ምስጥራዊ የአስመጪና ላኪ ደርጅት ፈጠሩለት፡፡ ይህውም አል ናስር ተሰኘ ህጋዊ መሰል አስመጪና ላኪ የንግድ ኩባንያ ማቋቋማቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይህ የደህንነቱ የንግድ ኩባንያ በአልጄሪያ፣በደቡብ የመንና በበርካታ የአረብና የአፍሪካ ሀገራት ነጻነት እንዲያገኙ በስውር መስራቱ ይነገራል፡፡የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳዮች የሚመለከተው ቢሆንም ፤ ጄነራል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት (GID) በበርካታ የአረብና የአፍሪካ ንቅናቄዎችን በመደግፍ እጁን አስገብቷል፡፡

ግብጽ በስለላና ደህንነት መዋቅሯ ውስጥ የብላክ ኦፕሬሽን (black operation) ”የጭለማ ዘመቻ” መምሪያ አላት፡፡ ”ብላክ ኦፕሬሽን” በመንግስታዊ ኤጀንሲ በምስጥር ወታደራዊ አሃድ ወይም ፓራሚሊተሪ ድርጅት (መደበኛ ያልሆነ ውትድርና ቀመስ አደረጃጀት) ወይም የግል ኩባንያዎች ወይም ቡድኖች የሚፈጽሙት ስውር ዘመቻ ነው፡፡

እንዲህ ያሉ ዘመቻዎች ”የጭለማ ኃይሎች ” የወጠኑትን ዘመቻ በሚስጥር የሚፈጽሙበትና ”ያልታወቁ ኃይሎች ” በሚል ለማምለጫ የሚጠቀሙበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡ የግብጽ የስለላና ድህንነት ተቋም ይህንን ዘመቻ እንደ መምሪያ አደራጅቶ በተለያዩ ሀገራት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

ከሀገር ውስጡ ኃይል ጋር የተቀናጀና በመመሳጠር ከፍተኛ ስልጠና የወሰደ ወታደራዊ አሃድ በፈጣን ማጓጓዣ የሀገሪቱን የየብስና የአየር ክልል ጥሶ በመግባት የወጠኑትን እቅድ አሳክተው የሚወጡበት እድሉ ዝግ አይደለም፡፡

የህውሀት ከፍተኛ አመራሮች የአቶ ስዬና አብረሃና የአቶ ስዩም መስፍን ቃለምልልስ ውስጥ ጦርነት ከተጀመረ በአካባቢው እጃቸውን የሚያስገቡ በርካታ የማይታወቁ ኃይሎች እንደሚኖሩ የገለጹት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ይህ ብዙ ምርመራ የሚጠይቅ ነው፡፡

ለማንኛውም ከላይ ያነሳሁትን የግብጽ ስለላና ደህንነት ተቋም ሚስጥራዊው የአል ናስር አስመጪና ላኪ የንግድ ኩባንያ እንደ እርሾ ሆኖ የአል ናስር ሞተር ካርን ጨምሮ በርካታ የማይታወቁ ግዙፍ የንግድ ተቋማትን በሽፋን እንደምትጠቀም ማስታወሱ ነጥብጣቡን በሚገባ ለማገናኘት መነሻ ይሆናል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top