Connect with us

ትሕነግ፥ “ገደልኩ” እና “አቆሰልኩ” የምትለው……

ትህነግ እንዴት በሀሰት ኢትዮጵያ ካላት ሰራዊት በላይ ገደልኩ እንዳለ የሕግ ባለሙያው ውብሸት ሙላት ከስር ባለው መሰረት ቁልጭ አድርጎ አጋልጦታል።
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ትሕነግ፥ “ገደልኩ” እና “አቆሰልኩ” የምትለው……

ትህነግ እንዴት በሀሰት ኢትዮጵያ ካላት ሰራዊት በላይ ገደልኩ እንዳለ የሕግ ባለሙያው ውብሸት ሙላት ከስር ባለው መሰረት ቁልጭ አድርጎ አጋልጦታል።

***

ትሕነግ፥ “ገደልኩ” እና “አቆሰልኩ” የምትለው የወታደር፣የልዩ ኃይል፣ ሚኒሻና ፋኖ ብዛት፤ ትሕነግ፤ ውሸት እንዴት እንደሚዋሽ እንኳን የማያውቅ የደረቀ ቡድን ነው!

(ውብሸት ሙላት)

ሀ)  ስለ ቁጥሩ አሰላል

ከዚህ በታች የቀረበው መረጃ ትሕነግ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የአገር መከላከያ ሠራዊቱን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችንና ሚኒሻዎችንና ፋኖን “ገደልኩና አቆሰልኩ” በማለት በትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲና በድምጸ ወያኔ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ያስተላለፋቸው መረጃዎች ናቸው፡፡ የመረጃዎቹን አወሳሰድ በሚመለከት ቅድሚያ የተሰጠው ለትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ሲኾን በትሕነግ ሥር በነበረበት ጊዜ (እስከ November 2020) እና መልሰው መጠቀም ከጀመሩበት ጊዜ ወዲህ ያሉት መረጃዎች ከእዚህ ጣቢያ ተወስደዋል፡፡ 

ይህ ጣቢያ በትሕነግ ቁጥጥር ሥር ባልነበረበት ወቅት ደግሞ ከድምፀ ወያኔ ተወስዷል፡፡ በመሆኑም ይህ ቁጥር ትሕነግ በሌላ ሚዲያ ያስተላለፈውን አላካተተም፡፡ ሁለቱም ጣቢዎች በድረ ገጻቸው (ዩቲዩብ) በጫኗቸው መረጃዎች ብቻ ላይ የተወሰነ ነው፡፡

መረጃዎቹ እንዳይደጋገሙ የተላለፉበትን ቀን፣ ጦርነት ተካሔደ የተባለበትን ቀናትና ቦታ  የተለያዩ መሆናቸውን በማጣራት ነው፡፡ ሰንጠረዡን ላለማጨናነቅና በቀላሉ እንዲነበብ ለማድረግ ሲባል እንጂ ጦርነቶቹ ተካሂደውባቸዋል የሚሏቸውን ጊዜና ቦታዎች፣ እንዲሁም በጦርነቱ የተሳተፉትን ማለትም “ገደልን፣ ደመሰስን፣አቆሰልን፣ከጥቅም ውጭ አደረግን፣ ማረክን” ያሏቸውን ክፍለ ጦሮች፣ ብርጌዶች፣ሻለቃዎች፣ ሻምበሎች መዘርዘር ይቻል ነበር፡፡

“ገደልን” የሚሉት በቁጥር ሳይሆን ክፍለ ጦርን፣ ብርጌድን፣ሻለቃን (ቦጦሎኒን) እና/ወይም ሻምበልን “ሙሉ በሙሉ ደምስሰናል” በሚል የተገለጹትን በሚመለከት የእያንዳንዳቸውን አደረጃጀቶች አማካይ የሠራዊት ብዛትን 5,000፣ 1,250፣350 እና 85 እንደቅደም ተከተላቸው በመውሰድ ነው የተሰላው፡፡ የአንድን ክፍለ ጦር “ሁለት ሦስተኛና በከፊል ደመሰስን” ያለውን ‘ግማሽ’ በማድረግ ተወስዷል፡፡

የኮማንዶ ብርጌድ ወይም ሻለቃ በውስጡ የሚይዘው የሠራዊት ብዛት ከመደበኛው ወይም እግረኛው በቁጥር ሊያንስ እንደሚችል የታወቀ ቢሆንም፤ ከጠቅላላ ድምሩ አንጻር ሲመዘን ተደመሰሱ የተባሉት እዚህ ግባ የሚባል ልዩነት የሚፈጥር ባለመሆኑ ድምሩን ለማስላት በመደበኛ ሠራዊቱ አንድ ብርጌድ ወይም ሻለቃ ከሚኖረው የወታደር ብዛት እንዲለይ አልተደረገም፤ተመሳሳይ ነው፡፡

ገደልን ወይም አቆሰልን የሚሉት “ከእዚህ በላይ/ልዕሊ” በሚል የተገለጹ ከሆነ፣ በትሕነግ ውሸት ላይ ተጨማሪ ግምት ላለማከል ሲባል ዝቅተኛውን ማለትም የመነሻ ቁጥሩ እንዳለ ተወስዷል፡፡

ስማቸው ሁለትና ሦስት ጊዜ በተደጋጋሚ የተገለጹ ክፍለ ጦሮችና የአማራ ልዩ ኃይል ሲኖር ስማቸው እንዳለ ሆኖ በድጋሜ ተደራጅተው ሊሆን ይችላል የሚለውን ከግምት በማስገባት ነው፡፡ በተረፈ ይህ ቁጥር የኤርትራ ሠራዊትን አያካትትም፡፡

የተላለፈበት ቀን በአውሮፓውያን አቆጣጠር የተጻፈበት ምክንያት ማመሳከር/ማረጋገጥ የሚሻ፣ ወይም ሌላ የሚዲያ ሥራ መሥራት የፈለገ አንባቢ በቀላሉ እንዲያገኘው በሚል ነው፡፡

ለ. “ብበርቃዊ መጥቃቲ…”

ጦርነት ነውና ከሁለቱም ወገን የሚሞትም የሚቆስልም መኖሩ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ ሌላው ሊያጠያይቅ የማይችለው ከነጭም በላይ የነጭ ነጭ ውሸት የትሕነግ ውሸት ነው፡፡ ከ 300 ሺ በላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ሚኒሻና ፋኖ ገድያለሁ፣ከ75ሺ በላይ ደግሞ ቁስለኛ አድርጌያለሁ ማለት ለወደፊት ውሸት እንዴት መዋሸት እንደሌለበት ማስተማሪያ የሚሆን ነው፡፡ አቆሰልን የሚሉት ብዛት እርግጠኛ ሆነው የሚናገሩት እንዴት እየቆጠሩት እንደሆነ፣ የትግሬ ‘ወታደራዊ ወሃቢ ቃል ገበረ ገብረጻድቃን’ ብቻ ይመስለኛል የሚያውቀው፡፡

 በነገራችን ላይ ዘጋቢዎቻቸውም፣ ዜና አንባቢዎቻቸውም፣ ገብረ ገብረጻድቃን፣ጌታቸው ረዳም፣ደብረፂዮንም እና ሌሎቹም ትሕነጎች የማይስቷቸው ወይም ዘወትር የሚጠቀሟቸው አገላለጾች አሏቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዷ በጣም የምታዝናና ናት፤ አንድም ሰው ቢገድሉ ወይም ቢያቆስሉ፣ወይም ተዋግተው ቢሸሹ እንኳን ሁልጊዜም “ብበርቃዊ መጥቃቲ”  ነው፡፡ መብረቅ በኪሳቸው ሸጉጠው የሚጓዙ እስኪመስል ሁልጊዜም መብረቃዊ ጥቃት ነው የሚፈጽሙት፡፡ እያለቁም “ውፈር ተበገስ… ሳይንሳዊ መብረቃዊ…” እያሉ እምቧለሌ ማለት፡፡

ከታች የቀረበውን መረጃ መነሻ በማድረግ ከተለያዩ የእሳቤ ማዕዘናት አንጻር በጣም በርካታ ትንታኔ መሥራት ይቻላል፡፡ ለአሁኑ ግን ጥሬ መረጃውን ብቻ እነሆ!

በነገራችን ላይ ትሕነግ ገደልኩና አቆሰልኩ ያለቺው ኢትዮጵያ አሁን ያላትን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ወደፊት የምታሠለጥነውም ጭምር ይመስላል፡፡ የሌለን ወታደር መግደልና ማቁሰል የሚቺለው ትሕነግ ብቻ ነው፡፡

ሐ) ትሕነግ “ገደልኩና አቆሰልኩ” የምትለው

በድምር!

~ትህነግ በአጠቃላይ  ከ219,903 በላይ ሰራዊት ገድያለሁ ብሏል!

~77 ሺህ  45 አቆሰልኩ ብሏል።

~ 12 ክ/ጦ፣  2 ከፊል ክ/ጦር፣ 8 ብርጌድ፣  4 ሻለቃ፣ 3 ሻምበል ሙሉ በሙሉ ደምስሻለሁ ብሏል።

በመግቢያው በተገለጸው አማካይ የሠራዊት ብዛት መሠረት የተሰላ ገደልኩና አቆሰልኩ ያለው ድምር= 76,655

~አጠቃላይ ትህነግ ገድያለሁና አቁስያለሁ ያለው ሰራዊት ብዛት= 381,103

ልብ በሉ። ኢትዮጵያ በአጠቃላይ 381103 ሰራዊት አለኝ አላለችም።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top