Connect with us
የፌ/ጠ/ዐ/ህግ

ህግና ስርዓት

ዘንድሮ ለ692 የፌደራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ

~ ዕድሉን ካገኙት ውስጥ 39ኙ ሴቶች ሲሆኑ 113ቱ ለከፋ የጤና ችግር የተጋለጡ ናቸው፣

በበጀት ዓመቱ ለ1,307 ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን የቦርድ ጽ/ቤቱ ከህግና ማስረጃ አንፃር ጥያቄዎቹን በመመርመር ለቦርድ አቅርቦ ቦርዱም በይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 840/2006 መሰረት የህዝብ፣ የመንግስትና የታራሚዎችን ጥቅም ከግምት በማስገባት ውሳኔ መስጠቱ ተገልጿል፡፡

ከአፈጻጸሙ ጋር በተያያዘ ገለጻ ያደረጉት የይቅርታ እና ምህረት ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘለቀ ዳለሎ ሲሆኑ በተገባደደው በጀት ዓመት ይቅርታ ሊደረግላቸው ይገባል ተብለው የተለዩ የፌደራል ታራሚዎች ማስረጃ ለቦርዱ የቀረበ መሆኑን ጠቅሰው ከቀረቡ ጥያቄዎች ዉስጥ በግል የይቅርታ ጥያቄ ያቀረቡ 70፣ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በመደበኛ መስፈርት በጥናት የተለዩ 120፣ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም የኮሮና ቨይረስ በመከሰቱ ምክንያት በወቅቱ ሳይቀርቡ የቀሩና በአመክሮ ሊፈቱ 1 ዓመትና ከዚያ በታች የቀራቸው 57፣ ሦስት ዓመትና ከዚያ በታች የተፈረደባቸው 92፣ የኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው 113፣ በዕድሜ መግፋት ምክንያት 17፣ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በታክስ ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው 3፣ የፌዴራል ታራሚዎች ሆነው ከኦሮሚያ ክልል በመደበኛ መስፈርት የቀረቡ 27፣ ከአማራ ክልል በመደበኛ መስፈርት የቀረቡ 11፣ ከደቡብ ክልል በመደበኛ መስፈርት የቀረቡ 7፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመደበኛ መስፈርት የቀረቡ 2፣ ከጋምቤላ ክልል በመደበኛ መስፈርት የቀረቡ 26፣ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በኤንባሲያቸው ጠያቂነት የቀረቡ 18 የውጭ አገር ዜጎች እና ከመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤት የቀረቡና ከሦስት ዓመት በታች ፍርደኛ የሆኑ 129 ታራሚዎች በድምሩ የ692 ታራሚዎች ማስረጃ ከአሳማኝ ምክንያቶች ጋር የቀረበ ሲሆን ጥያቄያቸው ተቀባይነተ አገኝቶ በመጽደቁ የይቅርታ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 48ቱ ከእስራት ፍርድ በተጨማሪ የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ በፍርድ ቤት በመወሰኑ የተጣለባቸዉን የ487,800 ብር መቀጮ እንዲከፍሉ የማድረግ ሥራም ተሰርቷል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የ615 ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ከቀረበው ማስረጃና ይቅርታ ከተጠየቀበት ምክንያት አንጻር ታይቶ ውድቅ በመደረጉ፣ ምክንያቱ ተገልፆ ለፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እና ለክልሎች ደብዳቤ ሲፃፍ ታራሚዎቹም በግልባጭ እንዲያቁት ተደርጓል የተባለ ሲሆን ይቅርታ ከተፈቀደላቸው ታራሚዎች ውስጥ 6ቱ ይቅርታ የተደረገላቸው በተሳሳተ ማስረጃ እንደሆነ በመረጋገጡ ይቅርታቸው ተሰርዞ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገቡ ስለመደረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 39ኙ ሴቶች ሲሆኑ 113ቱ ደግሞ ለከፋ የጤና ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በተያያዘ ጉዳይም ቦርዱ ከዚህ ቀደም የታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ተጣርቶ እንዲቀርብ የማድረጉ ተግባር ክፍተቶች የተስተዋሉበት በመሆኑ ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት በማሰብ የይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በሚል ርዕስ በተለይም በይቅርታ አሰጣጥና አፈፃፀም የሚታዩ ችግሮችና በጉዳዩ የሚሳተፉ አካላት ኃላፊነትና ተጠያቂነት፣ አንድ ታራሚ ይቅርታ ለማግኘት ማሟላት የሚገባው ጉዳዮች፣ ይቅርታ እንዲሰጥ የሚቀርቡ ማስረጃዎችን ትክክለኝነት ማረጋገጥ በሚቻልባቸውና መወሰድ ባለባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጥናት በማካሄድና በማጽደቅ ግልጽ የሆነ የአሰራ ሥርዓት በመዘርጋት ሥራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡(የፌ/ጠ/ዐ/ህግ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top