Connect with us

ዜናው ለእኛ ብስራት ለእነርሱ …

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው
አልጀዚራ

ዜና

ዜናው ለእኛ ብስራት ለእነርሱ …

ዜናው ለእኛ ብስራት ለእነርሱ …

– ሱዳን የግዛት ክልሏን ካልፈቀደች በግድቡ ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደማይቻል ዮርዳኖሳዊዉ ወታደራዊ ተንታኝ ጄኔራል ሂሻም ኩረይሳት ገለጹ።

– ጄኔራል ሂሻም ለአልጀዚራ በሰጡት ምላሽ ግብጽ በወታደራዊ ሃይል እርምጃ ለመዉሰድ የሱዳንን የአየር ክልል ካልተጠቀመች እንደማትችል ገልጸዋል።

-ሱዳን በሁለት ምክንያቶች ግብጽን እንደማትተባበር አስረድተዋል:-

1- ሱዳን ጥቅሟ ከአረብ ሊግ ይልቅ ከአፍሪካ ህብረተ ጋር መሆኑን

2- ግብጽ  (ሃላይብ ) የሱዳን ግዛት በመያዟ  በሱዳን ዘንድ እንደ ወራሪ የምትቆጠር መሆኑን ገልጸዋል።

– አሁን ግብጽ ያላት አማራጭ ከ በርኒስ ቤዝ መጠቀም ሲሆን ይህም የቀይ ባህርን አየር ክልል በመጠቀም የኤርትራን ፈቃድ በማግኘት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በመዝለቅ ግድቡን መድረስ ሲሆን ይህም 2170 km ሲሆን ኢላማ አጥቅቶ ለመመለስ ደርሶ መልስ 430 km ነዉ።

– ግብጽ ከፈረንሳይ የገዛቻቸዉ ራፋል F16 Su አዉሮፕላኖች 1900 km የመድረስ አቅም ብቻ እንዳላቸዉ አሰረድተዋል።

– ራፋል ወደ ኢትዮጵያ አየር ክልል ከገባ እና በከፍታ ከበረረ በህዳሴ ግድብ አካባቢ ባለዉ ሰፖይደር መቃወሚያ ቁጥጥር ስር እንሚወድቅ አስረድተዋል።

– አሁን ባለዉ ሁኔታ  እንኳን ቢቻል ግድቡን ሙሉ መምታት አደጋዉ የከፋ መሆኑን ይኸዉም ሱናሚ ተፈጥሮ ካርቱምን ጨምሮ ሱዳን ዉስጥ ቀዉስ እንደሚፈጠር አስጠንቅቀዋል።

– የሱዳን ተደራዳሪ ቡድን ቃል አቀባይ ዶ/ር ፉአድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር ሙሌት የምታካሄድ ከሆነ ኢትዮጵያ ላይ ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ እንደምትወስድ ገልጸዋል።

– በኢትዮጵያ በኩል ሁለተኛ ዙር የግድቡን ሙሌት መጀመሯን ለሱዳንና ለግብጽ ዛሬ ማሳወቋን አልጀዚራ ዘግቧል።

Aljazzera Mubasher

ትርጉም:- Abrar Mukhtar

05/07/2021

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top