Connect with us

ሲደመስሱ የነጻነት ሠራዊት፤ ሲደመሰሱ ንጹሃን፤ የትህነግ የፖለቲካ ድራማ!!

ሲደመስሱ የነጻነት ሠራዊት፤ ሲደመሰሱ ንጹሃን፤ የትህነግ የፖለቲካ ድራማ!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሲደመስሱ የነጻነት ሠራዊት፤ ሲደመሰሱ ንጹሃን፤ የትህነግ የፖለቲካ ድራማ!!

ሲደመስሱ የነጻነት ሠራዊት፤ ሲደመሰሱ ንጹሃን፤ የትህነግ የፖለቲካ ድራማ!!

(እሱባለው ካሳ ~ድሬቲዩብ)

የትህነግ ድራማ ቅጥ የለሽ መሆኑን እያየን ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ መራቡን የሚነግሩን አክቲቪስቶቻቸው የእርዳታ እህል ጭኖ የሚሄድ መኪና ሹፌር ግድያን አይኮንኑም፡፡ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብና የፖለቲካ ፍልስፍናቸው ለሰሚው ግራ ሆኗል፡፡

በተደጋጋሚ እንዳየነው ድል ሲሆን ጀግንነት ይባልና ድል ሲመቱ መልሰው ጭፍጨፋ የሚል ስም ይሰጠዋል፡፡ ሰሞኑን በትህነግ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚታዩት የጦርነት ጉሰማዎች ውሎ አድሮ ሌላ ሰብዓዊነት ኡኡታን እንደሚያስነሳ እሙን ነው፡፡

ጦርነት ከሆነ ስሙ ጦርነት ነው፡፡ ድል አድርገናል ብሎ የሚጨፍረው አፍቃሪ ህወሃት ከድል በኋላ ጀግንነትን አወድሶና የፈለገ መጥቶ ይግጠመን ብሎ ፎክሮ መልሶ ድል ሲመታና መቀመቅ ሲገባ ንጹሃንን መጨፍጨፍ ሲል ጦርነትን ሌላ ስም ይሰጠዋል፡፡

ሰላም መስበክ ሲሸነፉ ብቻ አይደለም፡፡ መከላከያ ዘወር ባለ ቁጥር ከተማ እየገቡ መዝረፍ ብቃትም ጀግንነትም አይደለም፡፡ ስርቆት አመሉ የሆነ ነጻ አውጪ ነጻ ወጥቶም መልሶ ለባርነት የሚዳረገው በስርቆቱ መሆኑ ያሳፍራል፡፡

በትግራይ የእርዳታ እህል የሚሰርቅን ነጻ አውጪ ምን አይነት ስም ልንሰጠው እንደምንችል ግራ እስኪገባን ቅሌቱ በዝቶብናል፡፡ እንዲህ ያለ ቅሌት የተሸከመ ሃይል መልሶ የእጁን ሲያገኝ ሰብዓዊነት የሚለው ሌላ ዘፈን ደግሞ መዘፈን ይጀመራል፡፡

የትህነግ ደጋፊዎች እጅ እግር በሌለው አጀንዳ መከራቸውን እያዩ ነው፡፡ መራባቸውን እና ሰው ሰራሽ ረሃብ መታወጁን እናሳምናችሁ ይሉናል፡፡ የእርዳታ እህል የሚሰርቅ ነጻ አውጪ ነኝ ባይ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ሲባሉ ግን አያምኑም፡፡

ትናንት ዘመቻ አሉላ ብለው ብዙ ነግረውናል፡፡ ዘመቻ ሀገርን ማዳን ሲታወጅ ግን ኡኡታቸው ገደብ የለውም፡፡ ጦርነት የገባ ቡድን እድሉም ውጤቱም የጦርነት ሜዳ ነው፡፡ ሲበተን ስለ ሰብዓዊነት እያወራ ሲያወድም ድልና ኩሩነትን እየሰበከ ሁለት ቦታ ሲረግጥ አይተነዋል፡፡

አሁንም በትግራይ ክልል እየሆነ ያለው ነገር የሰከነነ እና ገለልተኛ አካልን ይፈልጋል፡፡ የእርዳታ እህል ጭኖ መግባት ያስገድላል፡፡ የእርዳታ እህል ሸጣ መሳሪያ በመግዛት ለስልጣን ለበቃች ወንበዴ እርግጥ ነው የትግራይ ህዝብ መከራ ረሃብና ስቃይ ምንም ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ መከራው ቢበዛም ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የሚጓጓው ትህነግ እድሉን አስፍቶ እየተጠቀመ ነው፡፡ ከዚህ የባሳ ስቃይ በህዝቡ ላይ እንዲደርስ የቻለውን ሁሉ ማድረጉን ቀጥሏል፡፡ ረሃቡ ጸንቶ ጦርነቱ በርትቶ ህዝቡ ስቃዩ ከበረታ ደርግ የገጠመው ይገጥመንና ዳግም ለስልጣን እንበቃለን የሚሉ ሰካራሞች ሌላ ቅዠት ውስጥ መሆናቸው ታይቷል፡፡

ሰሞኑን በተደጋጋሚ ድል አደረገን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን አንበረከክን የሚሉ ዜናዎችን ሰምተናል፡፡ ነገ ደግሞ ለቅሶ እናደምጣለን፡፡ መልሰው ትግራይ ምን አደረገች ይሉናል፡፡ በመሳሪያ ብዛት ማለቃቸውንና ያለ አግባብ በመከላከያ መገደላቸውን ይነግሩናል፡፡ ጦርነት የሚያውጁ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ሆነው ይመጣሉ፡፡

አሁንም ሰላምና እፎይታ ካስፈለገ የትግራይ ህዝብ ዋነኛ ጠላቱ ስካር አደንዛዥ እጽና የስልጣን ጥማት ያሰቃየው የህወሃት ቡድን ነው፡፡ ያ ቡድን አደብ ካልገዛ ትግራይ ሰላም አትሆንም፡፡ ያ ቡድን በእያንዳንዱ የትግራይ ምድር ደም አፍስሶ የመኖርን እድሉን ማረጋገጥ የሚፈልግ ነውና፤

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top