Connect with us

የሱዳን ፖለቲከኞች እብደትስ እንዴት ሰንብቶ ይሆን ?!

የሱዳን ፖለቲከኞች እብደትስ እንዴት ሰንብቶ ይሆን ?!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የሱዳን ፖለቲከኞች እብደትስ እንዴት ሰንብቶ ይሆን ?!

የሱዳን ፖለቲከኞች እብደትስ እንዴት ሰንብቶ ይሆን ?!

  (ንጉሥ ወዳጅነው -ድሬቲዩብ)

  የኢፌድሪ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የህዳሴ ግድቡን በሚመለከት ከዚህ ቀደም በግብጽ ተይዞ የነበረው ግትር አቋም አሁን ላይ እየተለሳለሰ የመጣበትን ምክነያት ተናግረዋል ፡፡ ይህውም በቀዳሚነት ሁለተኛው  የግድቡ ውሃ ሙሌት ስራ እንደማይቀር በመረዳታቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በግድቡ የውሃ ሙሌት የተነሳ የውሃ ጉድለት እንኳን ቢከሰት ጉድለቱን የምንሞላበት አማራጭ ዝግጅት አድርገናል በማለት  የህዝቡን ይሁንታ ለማግኘት አስበው ማድረጋቸውን ነው የጠቆሙት ፡፡  

      እኛም የሱዳን ግራ ተጋቢዎችስ እንዴት ሰንብተው ይሆን ?! ብለን እንጠይቃለን ፡፡ እውነት ለመናገር ግድቡ ለሱዳን ህዝብ ጥቅም እንጂ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል ነው ፡፡ ይህን ደግሞ ከማንም በላይ የካርቱም ፖለቲከኞችና የውሃ ሙያተኞች ጠንቅቀው ያውቁታል ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን ሱዳናዊያን ከወላዋያ አቋም የማይወጡና የግብፅን  ተፅዕኖ መቋቋም የማይችሉ ሆነው ተቸግረዋል፡፡ ይባስ ብለው ከአገራችን ጋር ወደአልተፈለገ ፍጥጫ ለመግባት የተዳረጉትም የሶስተኛ አገር ፍላጎትን ለማርካት በመመኘታቸው ነው ፡፡

  ኢትዮጵያና ሱዳን ግን በምንም መስፈርት ወደ ጦርነት መግባት ያለባቸው አገሮች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያና ሱዳን መለስተኛ ውዝግብ እና ግጭቶችን በየማህሉ ቢያስተናግዱም በታሪክ ሚዛን ሲታዮ ህዝቦቻቸው ከልዩነታቸው ይልቅ አንድነታቸውን ለማጠናከር ሲሰሩ የኖሩ ናቸው ። ሁለቱ አገሮች በእምነት ፣ በባህልና ኢኮኖሚ ያላቸው ትስስርም ብዙ ተስፋ የተጣለበት ነው።

      ሱዳን አደጋ ላይ ስትወድቅ ኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆቿን ህይወት ገብራ የካርቱምን ህልውና ለማጽናት ብዙ ዋጋ መክፈሏ የትስስራችን አንዱ ማሳያ ነበር ። የሱዳን ህዝቦችም ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቻቸው ከፍተኛ አመኔታ እንዳላቸው ለአለም አረጋግጠዋል፡፡ በተለይ በአብዬ ግዛት ግጭት ተቀስቅሶ ለተባበሩት መንግስታት ሠላም አስከባሪ ጥሪ ሲቀርብ፣ ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች (ሱዳንና ደቡብ ሱዳን) በሙሉ ድምጽ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንዲገባ እና ሰላም እንዲያሰፍን መስማማታቸው አገራቱ በኢትዮጵያና በሰራዊቷ ላይ ያላቸውን እምነት ያሳዬ ነበር ፡፡

   ኢትዮጵያ ለሱዳን ሰላም ያላትን ጽኑ እምነት የሚያመላክት ትልቅ ፖለቲካዊ እርምጃ እንደነበርም አይዘነጋም ፡፡ በቅርቡ በሱዳን ተቀሰቀሶ በነበረው አመጽ የሱዳን ዜጎች የዳቦ ጥያቄ አንግበው ወደ ብጥብጥ ሲያመሩ፣ ጥያቄዎችን  በሰላም እንዲፈቱና በሱዳን የሽግግር ኃይሎች መካከል የአሸማጋይነት ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ ለሱዳን ባለውለታ እንጂ ልትወረር የሚገባት ባላንጣ አልነበረችም ፡፡ተወርራም አገራችን እስከአሁን ያሳየችው ትግዕስት የዘላቂ ጥቅም አሰላሳይነቷን የሚያሳይ ነው ፡፡

  ታዲያ ኢትዮጵያ እነዚህን ሁሉ ከጉርብትና በላይ የሆኑ ተግባራት ከውና ስታበቃ፣ ‘ሱዳን በዚህ ጊዜ ለምን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግራ ወረራ ፈፀመች?’ ካልን ውስጡን ገላልጦ መፈተሽ ተገቢ ይሆናል። በቅድሚያ ግን የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን መሬት መውረሩ መነሻው ህዝባዊ አለመሆኑን መረዳት ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት እድል ይሰጣል ።

እናም የዚህ ጉዳይ ባለቤቱ ማነው? ካልን፤ የሱዳን ሕዝቦችን የዳቦ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ፤ ኪሳቸውን በሙስና ያደለቡ የቀድሞ ስርዓት ተዋናዮችና  ነጋዴ የጦር አዛዦች መሆናቸውን ለማወቅ ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡

   በተለይም በሱዳን ጦር ኃይል ወስጥ አሁንም ድረስ በስልጣን ላይ ያሉ እና የአልበሽር የጡት ልጆች የራሳቸውን ጦር እሰከ ማደራጀት የደረሱ ናቸው ። ይህ ወታደራዊ ኃይል የአገሪቱን ሀብት አሟጦ ወደ ካዘናው ያስገባም ነው። 

አልፎም በግብፅ መንግስት የሚታዘዝ በመሆኑ የህዝብን ጥያቄ አቅጣጫ ለማሳትና ካይሮን ለማስደሰት ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ግጭት ለመፍጠር ትንኮሳዎችንና በግድቡ ስራም ላይ አደናቃፊ ሆኖ ለመውጣት ነው እየተሳከረ ያለው ፡፡ የአዛዡ የግብፅ ገታራ አቋም መለዘብ ሲጀመርስ ፣ ወደቀልቡ ይመለስ ይሆን ?! ወደፊት የሚታይ ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top