Connect with us

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ አሰራር እንዲቆም ተቃውሞ ተደረገ

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ አሰራር እንዲቆም ተቃውሞ ተደረገ
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ

ስፖርት

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ አሰራር እንዲቆም ተቃውሞ ተደረገ

በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ህገወጥ አሰራር እንዲቆም ተቃውሞ ተደረገ

~ ለተቃውሞ ከተሰለፉት መካከል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ይገኙበታል፣

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እያደረገ የሚገኘውን ህገወጥ እና አላግባብ የሆነ አሰራርን በመቃወም በቶኪዮ 2020 ሃገራችንን በአትሌቲክ የሚወክሉ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች፣ የቀድሞ አትሌቶች የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሌሎች ሃገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና  አሶሴሽን አመራሮች በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጽ/ቤት በግቢ ውስጥ በመግባት ስርዓት ባለው ሁኔታ በፀጥታ ኃይሎች በተገኙበት በኦሎምፒክ ኮሚቴው እየተካሄደ ያለው ከህግ ውጪ ያሉ አሰራሮችና አካሄዶች በጽኑ በመቃወም ድርጊቱን ባስቸኳይ እንዲቆምና የሚመለከተው አካል በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ኘረዝደንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉም ተቀላቅለው ታይተዋል።

እንደሚታወቀው በታህሳስ ወር በሃዋሳ በተደረገ ጉባኤ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ መስከረም ላይ ከቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ማግስት እንዲደረግ ቢወስንም ቢሾፍቱ ላይ በተጠራ ጠቅላላ ጉባኤ በባህርዳር ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዶ ምርጫውን ለማከናወን ቢንቀሳቀሱም በባህርዳር ማካሄድ ሲከለከሉ በትላንትናው እለት በሃዋሳ ለማድረግ ሞክረው የነበረውን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን እንዳይካሄድ በፀጥታ ኃይሎች ቢታገድም ለሊቱን ከሃዋሳ የተወሰኑ የክልል ኮሚሽነሮችንና የስፖርት ማህበራት እንዲሁም አሶሴሽኖችን ይዞ በዛሬው እለት በጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ድንኳን በመጣል በድብቅና በዝግ ህገ ወጥ ምርጫ አካሂዷል፡፡

ከዚህ ቀደም 13 የስፖርት ሃገር አቀፍ የስፖርት ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ተቃውሟቸውን ለዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ለሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት በጽሁፍ ማሳወቃቸው ይታወቃል፡፡

 

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top