Connect with us

አዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ይጀምራል

አዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ይጀምራል
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች

ዜና

አዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ይጀምራል

አዲሱ ለሚ ኩራ ክፍለከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ይጀምራል

በቅርቡ 11ኛ ክፍለ ከተማ ሆኖ የተዋቀረው ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከዛሬ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት እንደሚሰጥ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አበሰሩ ።

ክፍለ ከተማው በይፋ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለለሚ ኩራ ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈው፣ ክፍለ ከተማው በሙሉ አቅሙ ስራ መጀመሩን በይፋ አብስረዋል::

አዲሱ ክፍለ ከተማ የለውጡ ትሩፋት ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ የሚሰራው መንግስት የብልፅግና ጎዳናን ለማስቀጠል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል::

የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊሲዎችች በመንደፍ ተግባራዊ እንደሚደረጉ እና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች 6 ነባር ወረዳዎች እና አራት አዳዲስ ወረዳዎችን በማደራጀት የአካባቢውን ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top