Connect with us

መልስ ~ ለጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ

መልስ ~ ለጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

መልስ ~ ለጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ

መልስ ~ ለጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ

“አባቴ ካኪ ነበር የሚለብሰው!”

(ዶ/ር ትግዕስት መንግስቱ ኃ/ማርያም)

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግር ባለበት ዘመን አንድ ግለሰብ ምን ለበሰ ምን እልለበሰም የሚለው ንትርክ ውስጥ ባልገባ ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል በሚለው አስተሳሰብ የጠበቀ እምነት ስላለኝ ይህንን መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ።

መንግስቱ ኃይለማርያም ካኪ ሳይሆን ሀር ነበር የሚለብሰው ላልከው ውሸት መልስ  መስጠት ግዴታ ስለሆነብኝ ነው።

ጋሽ አዲሱን ኢንተርቪው ስታረገው ለሰነዘርከው ውሸት አዝናለሁ። የጋዜጠኝነት ethics የማይደግፈውና በማስረጃ ላይ ያልተመረኮዘ የስም ማጥፋት ድርጊት ነው።

ካኪ ነበር የሚለብሰው ። መልኩ ትንሽ የተለየበት ምክንያት ካኪውን በመልኩ ሳይሆን ገልብጦ ነበር የሚያሰፋው

ካኪው ሲመጣ ትንሽ ልጅ ነበርኩኝ፤ ነገሩ ስላልገባኝ ‘ አባዬ እኛም ካኪ እንለብሳለን?’ ስለው ካኪ መልበስ ብቻ አይደለም ለኢትዮጵያ ከጠቀመ ባዶ እግራችንንም እንሄዳለን ነበር ያለኝ።

ወቅቱ ከ1984 (Gregorian calendar) ረሀብ ነበር ።

የውጭ ምንዛሪ በጣም ችግር በነበረበት ጊዜ ነው

ራስን መቻል በሚል ስሜት የተነሳሱ ሀገር ወዳድ አብዮተኞች ህዝባችን እየተራበና እየተቸገረ የውጭ ምንዛሪ በከንቱ አይፈስም ነበር መነሻው። የምናመርተውን ነው የምንለብሰው። እንደ ሀገር ለልብስ ብለን የውጭ ምንዛሪ አናወጣም ፣ ራሳችንን  አለብን ።

ካኪ ብቻ መልበስ ሳይሆን ነዳጅም ቁጠባ የተደረገበት ጊዜ ነው የምናተርፈውን ውጭ ምንዛሪ ለህዝባችንና ለሀገራችን በሚበጅ መልኩ መጠቀም አለብን ብለው የተነሱትን አብዮተኞች ማቃለል ብልግና ነው። ካኪ ሳይሆን ሀር ነበር መንግስቱ የሚለብሰው  የሚል ጭንቅላት የሀገር ፍቅርና መስዋትነት ምን  ማለት እንደሆነ የማይገባው ጭንቅላት ።

ካኪ መልበስ ብቻ አይደለም ከዛ በላይ ለሀገሩ ብዙ መስዋትነት ለከፈለው አባቴ ክብርና ምስጋና!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top