Connect with us

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ ወሰነ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ ወሰነ
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

ዜና

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ ወሰነ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ ወሰነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማዋን የጽዳት ሰራተኞች ለማመስገን እና ክብር ለመስጠት ልዩ የምስጋና እና የምሳ መርሃግብር መካሄዱን ገልፀዋል።

ም/ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው “የሌሊት ጭለማ ፣ ብርድ ፣ ዝናብ ፣ ፀሃይ እና መጥፎ ሽታ ሳይሉ ለከተማችን ጽዳት ቀን ከሌሊት የሚተጉትን የጽዳት ሰራተኞች ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ልዩ የምስጋና እና የምሳ መርሃግብር አዘጋጅተን ማዕድ አብረን በልተን ፤ “የምናመሰግናችሁ ስለሚገባችሁ ነው!” ብለናቸዋል”ብለዋል።

“እነኝህ የከተማችን ያልተዘመረላቸው ጀግኖችን ማመስገን እና ክብር መስጠት ለሁላችንም ክብር ነውም” ነው ያሉት ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

የከተማ አስተዳደሩም ስራቸውን በማክበር ለጽዳት ባለሞያዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲዘጋጅ መወሰኑንም አስታውቀዋል ።  

የጽዳት ሰራተኞች 80% እናቶች በመሆናቸው ይህ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጋላጭነታቸውን ይቀንሳል ብለዋል። 

“ልፋታቸውን የሚመጥን ክብር እና ድጋፍ መስጠት ከሁላችንም የሚጠበቅ ስለሆነ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማሳሰብ እወዳለሁ” በማለት ም/ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።

(አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top