Connect with us

ዓለም አቀፍ የሸማቾች ቀን!!

ዓለም አቀፍ የሸማቾች ቀን!!
ተስፋ ለኢትዮጵያ የሸማቾች ማህበር

ማህበራዊ

ዓለም አቀፍ የሸማቾች ቀን!!

ዓለም አቀፍ የሸማቾች ቀን!!

ዓለም አቀፍ የሸማቾቸ ቀን  ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

“የፕላስቲክ ብክለትን እናስወግድ ” በሚል መሪ ቃል በአለም  ለ38ኛ ጊዜ ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ እንዲሁም በአዲስ አባበ ከተማ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በድምቀት ይከበራል።

የሸማቹ መብቶች

        

  1. መሠረታዊ ምርቶችንና አገልግሎቶችን የማግኘት መብት አለው።

2.ከአደጋ የመጠበቅ መብት አለው።

3.መረጃ የማግጀት መብት አለው።

4.አማራጭ የማግኘት መብት አለው።

5.ድምጽን የማሰማት መብት አለው።

6.መብቱ በተነካ ጊዜ ካሳ የማግኘት መብት አለው።

7.የማወቅ መብት አለው።

8.ሸማቹ ለመኖር እና ለመስራት የተመቸ አካባቢ የመኖር መብት አለው።

ሸማቾች ከላይ የተዘረዘሩት 8 መብቶች ቢኖሩትም የሚከተሉት 5 ግዴታዎች ተጥለውብቷል።

  1. ተግባራዊ  የማድረግ ግዴታ

2.የመተባበር ግዴታ

3.ማህበራዊ ኃላፊነት

4.ስለአካባቢ ማወቅ

5.ንቁ የመሆን ግዴታ

                              

ሸማቾች የሚደራጁበት  ምክንያት

1ኛ.ምርቶችና አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አማራጮች በመብዛታቸው እና ለግብይት አስቸጋሪና በመሆናቸው ለዚህም ሸማቹ ለጥራቱና በንግድ ተቋማት ላይ በመተማመን ብቻ ይሸምታል የእቃዎችን ጥራትና በጊዜ ወቅት ብቻ መለየት አስቸጋሪ ሆኖአል።ይህም ለአጭበርባሪ የንግድ ተቋማት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮአል።

2ኛ ስለ ምርትና አገልግሎት በቂ መረጃ ባለመኖሩ ሸማቹ ከግዚ በሃላ ባሉት ሂደቶች ምክንያት ተጨማሪ ይከፍላል ወይም ውድ ይሆናሉ። ይህን መረጃ ለመስጠት የተደራጀ ማህበር ያስፈልጋል።

3ኛ አሳሳች ማስታወቂያዎች መብዛት ።አዳዲስ ፍላጎት በመፍጠር ህጻናትን በሚያማልሉሉ ወጣቶችን በሚያነሳሱ ማስታወቂያዎች መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ በመበራከቱ

4ኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሸማቹን ግላዊ መብት በመጣስ ያለ ፍቃድ መረጃ መሰብሰብ ስራ በማካሄድ የሸማቹን ፍላጎት ፥ምርጫ እና ልምድ ማወቅ መረጃዎችን  ያለፍላጎት ለሌላ አካል አሳልፎ መስጠት በመበራከቱ

5ኛ  ከጊዜ ወደ ጊዜ ምርቶች ለተጠቃሚዎች ደህንነት አደገኛ እየሆኑ መምጣት ።አደጋ የሚያደርሱ ምግቦችና መድሀኒቶች ብዛት መጨመር እንደምሳሌ ይወሰዳሉ። ለዚህም የተበላሹ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች  ይካተታሉ ።

6ኛ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌላቸው የዋጋ መናር ከጊዜ ወደ ጊዜ በማጋጠሙ  በዚህም ሸማቹን እየተማረረ በመምጣቱ ።

7ኛ  አላአግባብ ዋጋ ለመጨመር ሲባል ነጋዴዎች እቃ መደበቅ ከመጋዘን ከሱቅ ከእይታ ማጥፋት በመበራከቱ።

 (ተስፋ ለኢትዮጵያ የሸማቾች ማህበር)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top