Connect with us

ስለሀገሬን

ስለሀገሬን
ሔኖክ ሥዩም

ባህልና ታሪክ

ስለሀገሬን

ስለሀገሬን

‹‹የጉዞ ማስታወሻ›› እንደ ሌሎች የታሪክ መዛግብት ሁሉ ከራሱ ባህርይ በሚመነጭና ከጸሐፊው ሁለንተናዊ አቋም የተነሳ እጅግ አስቸጋሪ ጠባይ እንዳለው ይነገራል፡፡ ይሄውም ጸሐፊው ተጉዞ የሚደርስባቸው ቦታዎችና ባህሎች አዲስ ስለሚተዋወቃቸው እንግድነቱ የተገለጠ ነው፡፡

በእንግዳ ዓይን የሚታይ አዲስ ዓለም ደግሞ ለመተርጎምም ሆነ ለመበየን የተመቸ አይደለም ወይም ብያኔው ስር ከሰደደ መረዳትና ምልከታ የመነጨ ስለማይሆን ተዓማኒነቱ አጠያያቂ ይሆናል፡፡ ሌላው የተጓዡ ዓላማና ነጽሮተ ዓለም የጉዞ ማስታዎሻውን ተገቢነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡

ይህን ሐሳብ ለማጉላት የምዕራቡ ዓለም አሳሾች የጻፏቸው ድርሳናት ለቅኝ ገዥዎች መስፋፋትና ለተገዢዎች ስሁት ውክልና (miss representation) ሰበብ መሆናቸውን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል:: ይሁንና ይህ አስቸጋሪ ጠባይ ሥነ ጽሑፋዊ ዘውጉ የሚሰጠውን ሁለንተናዊ ፋይዳ አላጎደለበትም፡፡

ዛሬም ‹‹የጉዞ ማስታዎሻ›› በስፋትና በምላት ታሪክን በመዘከርና በሌሎች ሰፊ አካዳሚያዊ ልምምዶች ውስጥ ስፍራው ብዙ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ሀገሬ የሚለው የሔኖክ ሥዩም ( Henok Seyoume Hagere) መጽሐፍ ለታሪክ ጥናት፣ ለባህል፣ ለማህበራዊ ግንኙነት፣ ለኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲያም ሲል ለጠንካራ ማህበረሰባዊ ተራክቡና ለተሰናኙ የወል እሴቶች መገንባት ከፍ ያለ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ሔኖክ እንዲህ ያለ ረብ ያለው ተግባር በመፈጸሙ ምስጋና ያንሰዋል፡፡ በተጨማሪም መጸሐፉን ሳነበው ከተጓዡ ተራኪ ጋር አብሬ መድከሜንና ከፍ ዝቅ ማለቴን ሳስብ “ሔኖክ ሥዩም ሆይ! ደግመህ ደጋግመህ ጻፍ” ማለቴን አልደብቅም፡፡

#አገኘሁ_አዳነ_ድልነሳሁ

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top