Connect with us

የጎርጎራ ፕሮጀክት ዲዛይን ይፋ ኾኗል፤ ኮይሻ ዛሬ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ዲዛይን ይፋ ኾኗል፤ ኮይሻ ዛሬ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
Fana Broadcasting Corporate S.C

ባህልና ታሪክ

የጎርጎራ ፕሮጀክት ዲዛይን ይፋ ኾኗል፤ ኮይሻ ዛሬ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ዲዛይን ይፋ ኾኗል፤ ኮይሻ ዛሬ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

ሹማምንት ሆይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ እናጨበጭባለን፤ እናንተ በተራችሁ እንደ አቅማችሁ የሚያስጨበጭብ ስራ ስሩ

(ሄኖክ ስዩም – ድሬ ቲዩብ)

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ከታሰበው አልፎ ተሳትፎ ታይቶበታል፡፡ ሦስት ቢሊዮን ብር አገኛለሁ ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሩት ዘመቻ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቦበታል፡፡ ወንጪን ኮይሻንና ጎርጎራን የሚያለማው ሁለተኛ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ቱሪዝም የመዳረሻ ልማት ትልቁ ምኞትም ትልቁ ውጤትም እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የጎርጎራ መዳረሻ ዲዛይን ይፋ ሆኗል፡፡ ዶክተር አብይ ሱሲኒዮስ የተመኛትንና ጣሊያን የናፈቃትን ጎራጎራ ሊያሳዩን አንዱን ጣጣ ጨርሰዋል፡፡ ደስ ብሎኛል፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ከባህር ዳር እስከ ጎንደር ግማሽ ቀን ይበቃዋል ተብሎ የሚላገጥበትን የጎብኚ መዳረሻ ልብም እግርም አስሮ የሚያስቀር ግዙፍ ሀሳብ እንደሆነ ገና ምጣዱም ሳይጣድ ያጠገበኝና ያመንኩበት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ኮይሻ ሄደዋል፡፡ ኮይሻ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ የተረሳው ዳውሮ እና ኮንታ አዲስ ዘመን መጥቶለታል፡፡ ለዚያ ከተፈጥሮ ታርቆ ለሚኖር ህዝብ ይህ ቢያንስበትን እንጂ አይበዛበትም፡፡ ከግድቡ ቀጥሎ ሀገር ተባብሮ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች በመሆናቸው ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ያስተሳስራሉ፡፡

ይሄንን ሳይ የሚቆጨኝ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ትከሻ ሆዱን እየሞላ እድሜውን የሚገፋ ሹም ነው፡፡ ሹማምንቱ በየተሰማሩበት ታሪክ ሰርተው ቢያልፉ ቢያንስ ለልጆቻችን የምትመች ሀገር ትኖረናለች፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ እናጨበጭባለን፤ እናንተ በተራችሁ ሌላ የሚያስጨበጭብ ስራ እንደአቅማችሁ ሥሩ፡፡

ኢትዮጵያ ችግሯ ብዙ ነው፡፡ አራት ኪሎ አስባ ብቻ አይፈታም፡፡ በየአካባቢው ብዙ ስራ አለ፡፡ ጠቅላዩ ተራራ ሲያለሙ ተራራ ማጸዳት ያቃተው ሹም እጁ እስኪላጥ ቢያጨበጭብ እንቅፋት እንጂ ስኬት አይሆንም፡፡ 

አሁንም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ መዳረሻ፣ የታሪክ አሻራ፣ የአበው ቅርስ፣ የባህል እሴታችን ብዙ ሥራ ይፈልጋል፡፡ ምን እያደርግን ነው የሚል ሹም ከሌለ እና ምን ሰርቼ ወጣሁ ብሎ የሚቆጭ አመራር ካልተፈጠረ እንዲህ ያሉ ስኬቶችን ለማጣጣምና ለመጠቀም በራሱ ችግር ይሆናል፡፡ እናም መንፈሱ በሀገር ይናኝ፡፡

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top