Connect with us

አድዋን ጋምቤላ ላይ ስንዘክረው፤

አድዋን ጋምቤላ ላይ ስንዘክረው፤
ሄኖክ ስዩም

ባህልና ታሪክ

አድዋን ጋምቤላ ላይ ስንዘክረው፤

አድዋን ጋምቤላ ላይ ስንዘክረው፤

እነሆ ባሮ ዳር ነኝ

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጋምቤላ ነው፡፡ በጋምቤላ ቆይታው 125ኛው የአድዋ ድል በዓል ላይ ታድሟል፡፡ አድዋን በጋምቤላ ስንዘክረው ሲል የበዓሉን አከባበር ከቆይታው ድባብ ጋር እንዲህ ያጋራናል፡፡)

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

ዛፍ እንደ ዣንጥላ ተዘርግቶልኝ ማንጎ ስር ነኝ፡፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ፡፡ የበርሃዋ ገነት ይሏታል፡፡ ባሮን አሻግሬ እያየሁ ነው፡፡ አሁን ጎድሏል፡፡ ሲሞላ የሚገማሸርበት ሆኜ ቡናዬን እጠጣለሁ፡፡ የመጣሁት አድዋ ድልን ልዘክር ነው፡፡ 

ቀን ሌላ ሲሆን ይሄንን ይመስላል፡፡

ባሮ ዳር አድዋን እዘክራለሁ፤ ምን ይገርማል? አድዋ እንኳን የባለቤቱ የባሮ፤ የኒጀር እኮ ነው፡፡ በቪክቶሪያ ፏፏቴ የሚጨፍር የጥቁር ሁሉ ድል፡፡ 

ይሞቃል፡፡ ሙቀቱ ከፍ ሲል የመጣሁ እንግዳ ነኝ፡፡ አዲስ አበባ ከዚህ 766 ኪሎ ሜትር ትርቃለች፡፡ አርባ ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሚደርስ ወቅታዊ አየር ንብረት ጋምቤላ የስራ ሰዓቷን ጭምር አሻሽላለች፡፡ 

ወደ ዋናው አዳራሽ ገባን፡፡ ምክር ቤቱ፡፡ የክብር እንግዶች ገብተዋል፡፡ 

መድረኩ ላይ ኪነት እየቀረበ ነው፡፡ ቀድሞ ወደ አዳራሹ ስገባ ታዳጊዎች ስለ አድዋ እየዘመሩ ነው፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በክብር እንግድነት ታድመዋል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ክብርት ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው የዕለቱ የክብር እንግዳ ናቸው፡፡ 

ታዳሚው አድዋን በጋምቤላ እያከበረ ነው፡፡ ጠዋት ተነስተን የአድዋ መታሰቢያ ፓርክን መርቀናል፡፡ ከተማዋ በዚህ መሰል ድባብ ደምቃለች፡፡ ባሮ ድልድይ በባንዲራ አሸብርቋል፡፡

በኢትዮጵያ ገላው የሚያስጉዝ የጀልባ ጎዳና ወንዝ ባሮ ነው፡፡ አንድ ኩንታል አሳ የሚተፋ ለጋስ ወንዝ፡፡ ጋምቤላ አባቷ ባሮ ነው፡፡ ኦፔኖ ይሉታል እነሱ፡፡ 

በሱ ብትታወቅም ረዣዥም ወንዞችን የተቸረች ባለጸጋ ምድር ናት፡፡ አልዌሮ፣ ጊሎና አኮቦ የተባሉት የኢትዮጵያ ወንዞች አድራሻቸው ጋምቤላ ነው፡፡

ጊዜ ቢኖረኝ ኝሙሉ ሃይቅ እሄድ ነበር፤ ታታ የተፈጥሮ ሐይቅ ደግሞ ሌላው መስህብ ነው፡፡ ቡረይና የዓለም ቅርሱ ብዝሃ ህይወት ስፍራ ይገኛል፡፡ 

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top