Connect with us

አድዋ የሰሜን ኢትዮጵያ አጀንዳ የሚመስላቸው ዩኒቨርሲቲ ያልሆኑ ብሔርሲቲዎች፤

አድዋ የሰሜን ኢትዮጵያ አጀንዳ የሚመስላቸው ዩኒቨርሲቲ ያልሆኑ ብሔርሲቲዎች፤
Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

አድዋ የሰሜን ኢትዮጵያ አጀንዳ የሚመስላቸው ዩኒቨርሲቲ ያልሆኑ ብሔርሲቲዎች፤

አድዋ የሰሜን ኢትዮጵያ አጀንዳ የሚመስላቸው ዩኒቨርሲቲ ያልሆኑ ብሔርሲቲዎች፤

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

ሰው እንዴት ከአባቶቹ ክብር ይሸሻል? እንዴትስ ከቀለሙ ክብር ይጎድላል? ዓለም አቀፋዊ ጸጋን ተቀብሎ ከመንደሩ ቅጥር መውጣትን እንደ አበሳስ ማየት እንደምን ያለ መረገም ነው? አዘንኩ፤

ይሄ ሰሞን የአድዋ ድባብ የሚናኝበት ነው፡፡ ይሄ ሰሞን አባቶች ስለ ምትቀጥለዋ ሀገር ላትቀጥል ህይወት የገበሩበት ፍቅር የሚገለጥበት ልዩ ወቅት ነው፡፡ አድዋ የማን ነው? አድዋስ ለማን ነው?

የሰሜን ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች አድዋን በተለያየ አግባብ የተለያየ ትኩረት ሰጥተው ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡ ፖለቲካው ሲጎትታቸው እየተጎተቱም ቢሆን የታላቁን ዕለት ክብር አላጎሉትም፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ዩኒቨርሲቲዎች አሏት፡፡

 ብዙዎቹ አድዋ ምናቸውም አይደለም፡፡ ያሉበት ሆነው ስለሆነው የሚሰሙት በመገናኛ ብዙሃን ነው፡፡ ደፋሮቹ ደግሞ ምክንያት አያጡም፤ አድዋን ሰሜነኛ ማድረግ፡፡ አድዋ ሰሜን የሆኑ የድፍን ኢትዮጵያ አቅጣጫ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ አድዋን እንደ አንዱ ተራ ቀን ለምን አዩት? ስማቸውን የተሸከመ ግብር ስሌላቸው ይመስለኛል፡፡ ቢሆንላቸውማ፤ አይደለም ስለ አድዋ፣ ስለ ጥቁር ሁሉ፣ ስለ ነጻነት ሁሉ፣ ባርነትን እንቢኝ ስለማለት ሁሉ፣ የተከፈለ የየትም ሀገር መስዋዕትነት ቦታ አግኝቶ የጉባኤያቸው መነሻ በሆነ፡፡

ግን ብሔርሲቲ ሲኮን ይሄ ሀሳብ ከቢድ ነው፡፡ ብሔር ሲቲዎች አይደለም አድዋን የሚያህል ግዙፍ አህጉራዊ ጌጥ ይቅርና ብሔራቸውን እንኳን መሸከም አይችሉም፡፡ የብሔር ባንዲራ ከፍ አድርገው መልሰው አንዱን ብሔር በየጎጡ ስልሳም መቶም ቦታ ከፍለው የሚያባሉ ናቸው፡፡

ዛሬ ያ ባይሆን ኖሮ የአድዋ ጥናትና ጉባኤ እንደ አንበሳ አውቶቢስ የዋና ከተማዋ ጉዳይ ባልሆነ ነበር፡፡ የሰሜን ኢትዮጵያ አጀንዳ ሆኖ ብዙ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ታላቁን ቀን ባላጎሉት ነበር፡፡

አድዋ ምናችንም አይደለም ብንል የአባቶቻችን ክብር እናዋርዳለን፡፡ አድዋን ከፍ ባናደርገው የምንነቅፋቸውን አባቶች ክብር አናዋርደውም፡፡ አድዋ የሁላችን ስምና የጭቆና ነውር ሥርየት ነው፡፡

ጠንካራ ህዝቦች ብንሆን ዛሬ ከምድራችን እስከ ደርባን ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በአድዋ መንፈስ በተጥለቀለቁ ነበር፡፡ የማሊ ጎዳናዎች፣ የኪጋሊ አደባባዮች፣ የናይሮቢ መንገዶች፣ የዳሬሰላም አዳራሾች፣ አድዋን አድምቀው በዘከሩ ነበር፡፡

እኛ ደካማ ባንሆን፤ እኛ ባቢሎን ባንሆን ዛሬ ጁሃንስበርግ አድዋን በዘመረች፣ ኬፕታውን ሰንደቃችንን ከፍ ባደረገች፤ አፍሪቃ ስማችንን ጠርታ፣ በአፍሪቃ ተጠርተን፣ በእኛ በተጠራች፡፡ ግን እኛ ከሰፈራችን አልወጣንም፡፡

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top