Connect with us

በትግራይ በተቋማት ላይ ብቻ 3 ቢልየን ብር ኪሳራ ደርሷል

በትግራይ በተቋማት ላይ ብቻ 3 ቢልየን ብር ኪሳራ ደርሷል
ኢዜአ

ዜና

በትግራይ በተቋማት ላይ ብቻ 3 ቢልየን ብር ኪሳራ ደርሷል

በትግራይ በተቋማት ላይ ብቻ 3 ቢልየን ብር ኪሳራ ደርሷል

የህወሃት ጁንታ በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በሰሜኑ የሀገሪቱ  ክፍል በሚገኙ ታላላቅ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ከአገልግሎት ይገኝ የነበረ  ከ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ተቋማት እንዲያጡ ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጁንታው የህወሃት ቡድን የሀገሪቱን ዋና ዋና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ታላላቅ የመሰረተ-ልማት አውታሮች ላይ ባደረሰው ጥቃት በሀገር ሀብትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትና የመንግስት ተቋማት ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በኢትዮ-ቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በዚህ መሰረት በአካባቢው በሚገኙ የኢትዮ-ቴሌኮም መሰረተ-ልማቶች ላይ ጁንታው ባደረሰው ጉዳት ተቋሙ ማግኘት ከሚገባው 1 ቢሊዮን 370 ሚሊዮን 828 ሺህ 689 ብር ከ35 ሳንቲም በላይ ማጣቱ  በምርመራ መረጋገጡን አመልክቷል።

በተጨማሪም በተቋሙ ላይ ከ39 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ የተፈፀሙ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፍ መቻሉ ጠቅሷል።

በተመሳሳይ በሰሜን በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ-ልማቶች ላይ ጁንታው ባደረሰው ጉዳት ከ 329 ሚሊዮን 167 ሺህ 524 ብር በላይ ማጣቱ ተረጋግጧል።

በዚሁ ጥቃት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወልቃይት፣ በማይጨው፣ በአላማጣ እና በአሸጎዳ መቀሌ ሰብስቴሽኖች ላይ ውድመት የደረሰ መሆኑን የገለጸው ኮሚሽኑ፤ “በእነዚህ ንዑስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የምርመራ ቡድኑ በገንዘብ መጠን አስልቶ ወደፊት ይገልጻል” ብሏል።

በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ላይ ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት 14 ሚሊዮን 49 ሺህ 70 ሊትር ነዳጅ ከመቀሌ ነዳጅ ዴፖ በህገ-ወጥ መንገድ ተቀድቶ በመወሰዱ ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን 258 ሚሊዮን 190 ሺህ 998 ብር ከ64 ሳንቲም ማጣቱ በምርመራ እንደተረጋገጠ  ኮሚሽኑ ገልጿል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት በባህርዳርና በጎንደር ኤርፖርቶች ላይ የተተኮሰ ሮኬት በመሰረተ-ልማት ላይ 43 ሚሊዮን 349 ሺህ 784 ብር የሚገመት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በረራ ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አክሱም፣ መቀሌ፣ ሁመራ፣ ደሴ፣ ላሊበላ፣ ሰመራና ሽሬ ባለመደረጉ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 147 ሚሊዮን 640 ሺህ 223 ብር ከ97 ሳንቲም ገቢ ያጣ ሲሆን ሁለቱ ድርጅቶች በድምሩ 190 ሚሊዮን 990 ሺህ 8 ብር የሚገመት ገንዝብ ማጣታቸውን ጠቅሷል።

በሌላ በኩል ጁንታው  በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኛ የሆኑትን የተለያዩ ግለሰቦች በመጠቀም በወቅቱ የትግራይ ክልል መንግስት የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ በነበረው በዶክተር አብርሃም ተከስተ ትእዛዝ ሰጪነት በአንድ ቀን ብቻ በህገ-ወጥ መንገድ 800 ሚሊዮን ብር አውጥተው የወሰዱ መሆኑ በምርመራ እንደተረጋገጠ አመልክቷል።

ከዚህ ባንክ የወጣው ገንዘብ የት እንደደረሰ ወደ ፊት ምርመራው ሲጠናቀቅ የሚገለጽ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጠቁሟል።

“በአጠቃላይ ጁንታው የህወሃት ቡድን በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በሰሜኑ የሀገሪቱ  ክፍል በሚገኙ ታላላቅ መሰረተ-ልማቶች ላይ  ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ከአገልግሎት ሊገኝ የሚገባ ከ 2 ቢሊዮን 949 ሚሊዮን 177 ሺህ 220 ብር በላይ ተቋማቱ እንዲያጡ አድርጓል” ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አመልክቷል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top