Connect with us

ኮሚቴው፤ በጀጎል አከባቢ የሚስተዋለው ሕገ-ወጥ ግንባታ እንዲቆም አሳሰበ

ኮሚቴው፤ በጀጎል አከባቢ የሚስተዋለው ሕገ-ወጥ ግንባታ እንዲቆም አሳሰበ
ተስፋሁን ዋልተንጉስ~ ሕ/ተ/ም/ቤት

ባህልና ታሪክ

ኮሚቴው፤ በጀጎል አከባቢ የሚስተዋለው ሕገ-ወጥ ግንባታ እንዲቆም አሳሰበ

ኮሚቴው፤ በጀጎል አከባቢ የሚስተዋለው ሕገ-ወጥ ግንባታ እንዲቆም አሳሰበ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የሐረር ጀጎል ግንብ አከባቢ የሚስተዋለው ሕገ-ወጥ ግንባታ እንዲቆም፣ የክልሉን መንግስት አሳሰበ፡፡

ኮሚቴው ይህን የአሳሰበው፤ ሰሞኑን በሐረሪ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ የመንግስት ተቋማት የመስክ ምልከታ በአደረገበት ወቅት ነው፡፡ በዚህም ኮሚቴው በቅርስነት በተከለለው የጀጎል ግንብ አከባቢ ሕገ-ወጥ መኖሪያዎች እና ቤተ-እምነቶች መገንባታቸውን አረጋግጧል፡፡  

በጀጎል ግንብ ውስጥ ቁጥራቸው ከ80 የሚበልጡ መስጂዶች እና ከሁለት ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደሚገኙ ከተደረገለት ማብራሪያ የተረዳው ቋሚ ኮሚቴው፤ በቅርሱ ቅጥር ግቢ ከሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለተወሰኑት ምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ተሰጥቷቸው መልቀቃቸውን አስተውሏል፡፡ እንደዚሁም ነባር ቤቶች ደግሞ ሙዚዬም እና የዕደ-ጥበብ መሸጫ መደረጋቸውንም ተገንዝቧል፡፡

በሐረር ከተማ ምቹ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴሎች በአለመኖራቸው እና በኮቪድ-19 ምክኒያት የቱሪስት ፍሰቱ እንደቀነሰ ከባለሙያዎች ገለጻ ኮሚቴው ተረድቷል፡፡ በሌላ በኩልም፤ የቅርስ አያያዝ እና ጽዳት ጉድለት እንዳለው፣ የሐረር ግንብ አምስቱም በሮች ገላጭ ነገር እንደሌላቸው እና የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠባቸው አረጋግጧል፡፡ 

የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ አቶ ኢዶሳ አዱኛ በሰጡት ግብረ-መልስ፤ በቅርሱ አከባቢ የዕደ-ጥበብ ውጤቶች መሸጫ ቤቶች መከፈታቸውን፣ ሙዚዬሞች በሁሉም ቀናት ክፍት መሆናቸውን እና የአልተፈቀደ ግንባታ እንዳይካሄድ የተጀመረውን ቁጥጥር በጥንካሬ አወድሰዋል፡፡

በአንጻሩ ቅርሱን ከማስተዋወቅ፣ በቱሪዝም ዘርፉ ኢንቨስተሮችን ከመሳብ፣ በቅርሱ አከባቢ  ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን በተሟላ አኳኋን ከማስቆም እና ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር  አኳያ፤ ክፍተቶች መኖራቸውን የተከበሩ አቶ ኢዶሳ አመላክተዋል፡፡

የክልሉ የባሕል፣ ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን በበኩላቸው፤ የቱሪስት ፍሰቱ እነዲጨምር ታስቦ ከሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነ ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡ ለቱሪስቶች ምቹ ማረፊያ እንዲኖርም፤ በከተማዋ ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎችን ለመገንባት ዕቅድ መያዙንም አስታውቀዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በተጨማሪም፤ የሴቶችን፣ የሕጻናትን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት  እንዲሁም የክልሉን የማኅበራዊ ዘርፍ እንቅስቃሴ በተመለከተ ጉብኝት አካሂዷል፡፡ ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት፣ የሕጻናትን ደህንነት እና ጤናን ለመጠበቅ እንዲሁም ለግብረ- ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ከማድረግ አኳያ የተከናወኑ ተግባራት የተሻሉ መሆናቸውን አስተውሏል፡፡  

ኮሚቴው በአንጻሩ፤ ወጣቶች ከተደራጁ በኋላ ሥራ አለመጀመር፣ የተፈቀደው ተዘዋዋሪ ፈንድ ተደራሽነቱ እና የወጣቶች የምልመላ ሂደት ችግር እንዳለው፣ በክልሉ ገጠራማ ክፍሎች የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ አናሳ መሆኑን እና የአለዕድሜ ጋብቻ በአንዳንድ ቦታዎች መከሰት፤ ክፍተት የሚስተዋልባቸው ዐበይት ጉዳዮች መሆናቸውንም አመላክቷል፡፡

በማኅበራዊው ዘርፍ የጎዳና ተዳዳሪዎችን አሰልጥኖ ወደ ሥራ የማስገባት እና ወደ ቤተሰብ መቀላቀል መቻሉ፣ ለችግር ለተጋለጡ አረጋውያን ድጋፍ መደረጉ እንዲሁም በአሠሪ እና ሠራተኞች መካከል የሕብረት ስምምነት መቋቋሙ፤ በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን ኮሚቴው ተገንዝቧል፡፡

በሌላ በኩልም ትምህርት ቤቶች ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የአካትቶ ትምህት አሰጣጥ ተደራሽ የአለመሆን፣ የአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ አስገዳጅ አለመሆኑ እንዲሁም፣ የሴቶች እና ሕጻናት የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች የመዋቅር ችግራቸውን በክፍተት ገምግሟል፡፡

የክልሉ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አዲስ አለም በዛብህ በበኩላቸው፤ የሴቶችን ዕኩልነት ለማረጋገጥ በየመሥሪያ ቤቱ የሴት አመራር ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ብድርም የተመቻቸላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው  ክፍተቶች እንደሆኑ በሁሉም ዘርፎች ያመላከተንን በግብዓትነት በመውሰድ፤ በየደረጃው ችግሮችን ለማረም ሁለንተናዊ ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

(ተስፋሁን ዋልተንጉስ~ ሕ/ተ/ም/ቤት)

 

 

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top