Connect with us

ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና ፤ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ

ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና ፤ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ
አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ኢኮኖሚ

ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና ፤ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ

ባለፉት 27 ዓመታት በንግዱ ዘርፍ እኩል የሆነ የተሳትፎ ዕድል አልነበረም ” አቶ ክቡር ገና ፤ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ

 

 ባለፉት 27 ዓመት በነበረው የንግድ ሥርዓት እኩል የሆነ የተሳትፎ እድል እንዳልነበረ የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።የህወሓት ጁንታው ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር ጠቁመዋል ።

ሥራ አስኪያጁ አቶ ክቡር ገና በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፣ ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ፍትሐዊ ተሳትፎ ያላቸው የንግድ ድርጅቶች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ አልነበረም ።

ጉዳዩ ዛሬ እንደ አዲስ ይነሳ እንጂ በጉዳዩ ላይ ብዙ ተብሏል፡፡ለሕዝብም አዲስ ነው ብለው እንደማያምኑና እርሳቸው ቀድሞ የንግድ ምክር ቤት በአሁኑ ደግሞ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ተብሎ የሚጠራው ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ በማህበራቸውም ሆነ በተለያየ አጋጣሚ ሁሉ ለግሉ ዘርፍ ከአድሎ ነጻ የሆነ አሰራር እንዲኖር ክፍተቶችን በማሳየት ብዙ ርቀት መሄዳቸውን አስታውሰዋል። ሰሚ ባለመኖሩ እኩል ተሳትፎ ሳይፈጠር አሁን ላይ መደረሱን አመልክተዋል ፡፡

ለንግድ ድርጅቶች መቋቋም ዋና መሰረቱ አድሎ የሌለበት ምቹ አሰራር መዘርጋት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር፤ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጁንታ ቡድን የሆኑ አካላት ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ባልተገባ መልኩ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ድጋፍ ያገኙ እንደነበር አመልክተዋል።

በቦርድ ስም የሚሰየሙ የመንግሥት ኃላፊዎች እነዚህ የንግድ ድርጅቶች፣ መረጃ እንዲያገኙ ፣ከባንክ በፈለጉ ጊዜ መበደር እንዲችሉ፣ ብድር በወቅቱ ለመመለስ እንዳይገደዱ የሚያደርግ አሰራር የተዘረጋበት ሥርዓት እንደነበር ገልጸዋል።

ይህ አይነቱ አሰራር ለብዙዎች አዲስ እንዳልሆነና ሲተችም እንደነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ ይህም የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እንደጎዳውና ከውድድር እንዳወጣው አስታውቀዋል ። የንግዱ ማህበረሰብ ከራሱ አልፎ ለሀገርም ሚናውን እንዲወጣ አድርጎታል ከተፈለገ ፍትሐዊ አሰራርን ማስፈን እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

መንግሥታት የሕዝብን ጥቅም እናስቀድማለን ቢሉም ይህንን ቃላቸውን በተግባር ሲያውሉት አለማየታቸውን የጠቆሙት አቶ ክቡር፤የራሳቸው ጥቅም የሚያሸንፋቸው መንግሥታትን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል፡፡ችግሩ ዓለምአቀፋዊ ቢሆንም አፍሪካ ላይ ባለው የአቅም ውሱንነት ችግሩ የከፋ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በችግሮች ዙሪያ በተለያዩ ወቅቶች በሚመቻቹ መድረኮች ማህበሩ የሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች ተቀባይነት እንደሌላቸውና የሚደመጥም እንዳልነበር ያመለከቱት አቶ ክቡር ፣ አንዳንዶች ከሚፈልጉት ጋር ተነጋግረው በሚፈልጉት መንገድ ጉዳያቸውን ማስጨረስ የሚችሉበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ማህበራትም ሆኑ መንግሥታት ሚናቸው የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለክፍተቶች መፍትሄ መስጠት እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ክቡር ፣ ባለፉት 27 ዓመታት ይህ ሲሆን አልታየም ፤ የንግድ ድርጅቶች ባልተገባ መንገድ ከውድድር ውጪ መሆናቸውን አስታውቀዋል። የንግድ ድርጅቶች ከማነቆ የተላቀቁ አለመሆናቸውንም አመልክተዋል፡ (አዲስ ዘመን)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top