Connect with us

“በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የአካበቢው አስተዳደር ያውቃል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 

“በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የአካበቢው አስተዳደር ያውቃል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
አብመድ

ዜና

“በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የአካበቢው አስተዳደር ያውቃል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 

“በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የአካበቢው አስተዳደር ያውቃል” የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን 

 

የአማራ ሕዝብ በትህነግ የግፍ አገዛዝ ማንነቱን ተነጥቋል፤ የውሸት ታሪክ ተዘርቶበታል፤ የሚኮራበት መሪ እንዳይኖረው ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ወራሪው ትህነግ በአማራ ክልል የሚገዳደራት የፀጥታ ኃይል እንዳይኖራትም ያላደረገችው ጥረት አልነበረም፡፡ አማራ ከነብሱ አብልጦ በሚወዳት ሀገሩ፣ ደምና አጥንት በገበረላት መተኪያ የሌላት ኢትዮጵያ እንደሻው እንዳይኖርም አድርጋለች፡፡ 

በወቅታዊ ጉዳይ ከአብመድ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ካሁን ቀደም የአማራ ፖሊስና ልዩ ኃይል ዋጋ የለህም ተብሎ አንገቱን እንዲደፋ ተደርጎ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡ አሸባሪው ትህነግ የአማራ ሕዝብ የራሱ የፀጥታ ኃይል እንዲኖረው አይፈልግም ነበርም ብለዋል፡፡ የፀጥታ ኃይል የሕዝብ ምልክት፣ መከበሪያና ግርማ ሞገስ እንደሆነ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ገልጸዋል፤ ይህ ግርማ ሞገስ እንዳይኖረው ይፈለግ እንደነበር ነው የተናሩት፡፡ 

“የአማራ ልዩ ኃይል በሚል ተጠሩ እንጂ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ መኖር አለባት” ብለዋል፡፡ ብሔር ብሔረሰቦች ኢትዮጵያ ከሌለች መኖር እንደማይችሉም ነው ያመላከቱት፡፡ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዋስትና መሆኗንም አንስተዋል፡፡ አሁን ባለው አስተዳደራዊ ህጋዊነት በቅርፅ የአማራ ልዩ ኃይል ይባል እንጂ በይዘት የኢትዮጵያ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ 

ትህነግ ከወራት በፊት ከዋጃ ጀምሮ እስከ ሁመራ ድረስ ያደርጋቸው በነበሩ እንቅስቃሴዎች ለጦርነት የተዘጋጀ እንደነበር አመላካች መሆኑን አብነት ጠቅሰዋል፡፡ 

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተነካ ሲባል የአማራ ሕዝብ በአንድነት መነሳቱንም ጠቅሰዋል፡፡ “የተገፋህ ስትሆን ከተገፉት ጋር ትቆማለህም” ሲሉ ነው ሁነቱን የገለጹት፡፡ 

“ሀገር እንዳይፈርስ፣ መጥፎ ታሪክ እንዳይሰራ፣ ጥቂቶች ባጠፉት ሁላችንም እንዳንሳሳት እንጂ የምንታገሰው መተከል ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ አሰቃቂ ነው፤ ነብሰጡር ሆዷ ተቀዶ ሕጻን ወጥቶ የሚበላበት፣ ሰው በቀስት እየተመታ የሚገደልበትና አረማኔያዊ ድርጊት የሚፈፀምበት ነው፤ ይህን ግፍ ኢትዮጵያዊያን ማወቅ አለባቸው” ሲሉ አማራ በአማራነቱ ብቻ የተፈጸመበትን ግፍ በአብነት አንስተዋል፡፡ 

በመተከል እየተፈፀመ ያለውን ግፍ የአካበቢው አስተዳደር እንደሚያውቅ ነው የተናገሩት፡፡ አስተዳደሩ ተጠያቂም እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡ አካባቢውን በማስከበር በኩል ለፌደራል መንግሥት እያመለከቱ እንደሆነ ነው የገለጹት ኮሚሽነር አበረ፡፡ 

በመተከል ላይ ማንም ሰው መኖር እንዲችል እና ይህንን የሚከለክል ካለ እስከመጨረሻው እንደሚታገሉት አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅንጂት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን የተሰነዘረበትን ጥቃት በብቃትና በጀግንነት በመመከት፣ ሕዝብና ሃገርን የታደገበት መንገድ ታሪክ የማይረሳው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ 

ልዩ ኃይሉ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከማንም ቀድሞ በመድረስ የታፈኑትን በማስለቀቅ፣ የትህነግን አሸባሪ ቡድን ጉዞ በመግታትና በመደምሰስ አስደናቂ ጀብዱ መፈፀሙ አይረሴ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡(አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top