Connect with us

የመተከል ግጭት በቅርቡ ይቋጫል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

የመተከል ግጭት በቅርቡ ይቋጫል – አቶ አሻድሊ ሃሰን
Ethiopian News Agency

ዜና

የመተከል ግጭት በቅርቡ ይቋጫል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

የመተከል ግጭት በቅርቡ ይቋጫል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

 በጁንታው ቡድን ላይ ህግን ለማስከበር በተጀመረው እርምጃ የመተከል ግጭትም በቅርቡ አብሮ እንደሚቋጭ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ተናገሩ፡፡

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል  የተዘጋጀ የክብር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ በአሶሳ እና ሠመራ ሎጊያ ከተሞች ተከናውኗል፡፡

በአሶሳ በተከናወነው ሥነ-ሥርዓት የተገኙት ርዕሰ መሰተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እንደተናገሩት፤ የህወሓት ጁንታ ቡድን ሀገሪቱን ለማተራመስ በጠነሰሰው ሴራ በመተከል ዞንም ላለፉት ሁለት ዓመታት ጥፋት ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

“የጁንታው ሴራ የመንግስትን አቅም በማዳከም ሀገርን መበታተን ነው” ያሉት አቶ አሻድሊ፤ የበርካታ ዜጎች ሕይወት አለአግባብ እንዲጠፋ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ህግን ለማስከበር በመተከል በተወሰደው እርምጃ ትናንት ብቻ 20 የህወሃት የጥፋት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

የጁንታው ቡድን አባላት በመተከል ኢንቨስትመንትን ከለላ በማድረግ ሰፊ መሬት እንደወረሩ አመልክተው፤ በተለይ በክልሉ ኢትዮጵያዊያን እየገነቡት የሚገኘውን የህዳሴ ግድብን ማስተጓጎል ደግሞ ዋነኛ ግቡ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ልዩ ሃይልና ህብረተሰቡ የጁንታውን ሴራ ለማክሸፍ ተቀናጅተው በመስራት ተልዕኮ አስፈጻሚዎች ከዞኑ ህዝብ የመነጠል ሥራ እያካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል ዛሬ በተከናወነው የክብር ሥነ-ሥርዓት የጁንታውን መሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህግ በማቅረብ የሚወሰደው እርምጃ ለሠራዊቱ አቅም እንደሚሆን አቶ አሻድሊ ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በጁንታው ቡድን ላይ ህግን ለማስከበር የጀመረውን ስራ በክልሉ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤ የሀገር መከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ሃይል እስከ ህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top