Connect with us

“የተፈፀመብን ክህደት አሳዝኖናል”

"የተፈፀመብን ክህደት አሳዝኖናል"
የፌ/ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት

ዜና

“የተፈፀመብን ክህደት አሳዝኖናል”

“የተፈፀመብን ክህደት አሳዝኖናል”

~ ከአፈና ያመለጡ የፌደራል ፖሊስ አባላት

 

በትግራይ ክልል መቀሌ ሀራ ገበያ ዓዲ ጉደም ምድር ባቡር ፕሮጀክት በሚጠብቁት ላይ ከተፈጸመ ጥቃት የተረፉት ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት አዲስ አበባ ከተማ ገብተዋል፡፡

የህዝብና መንግስት መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ከ10 ዓመታት በላይ መቆየታቸውን የገለጸው ዋና ሳጅን ድረስ ስንሻው የተለመደዉን መደበኛ የጥበቃ ስራችን እያከናወን በነበርንበት ወቅት በፕሮጀክቱ ባሉ ሳይቶች ላይ የነበሩ የስራ ባልደረቦቻችንን ትጥቅ በማስፈታት፣ አፍነውና እጃቸውን በካቴና አስረው ወደ መቀለ ሲወስዷቸው እጃችንን ከምንሰጥ ብለን ወደ ጫካ በመግባት ለሚተኮስብን ተኩስ ምላሽ በመስጠት ለማምለጥ ችለናል ብለዋል፡፡

እኛ ለአንድ ብሔር የቆምን ሳይሆን ከሁሉም ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተውጣጣንና ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድነት ስንጠብቅ የኖርን በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሀገር ክህደት ይፈጸምብናል ብለን አልጠበቅንም ነበር በማለት ገልጸዋል፡፡

የታፈኑ አባሎቻችንን ለማስለቀቅ ብንሞክርም ከአቅማችን በላይ በመሆናቸውና እኛንም ለማስቀረት ከፍተኛ የሆነ ቶክስ ስለ ከፈቱብን ለጽንፈኛው ቡደኑ እጅ ከምንሰጥ በማለት ለሶስት ቀናት የሚበላና የሚጠጣ ባልነበረበት በበረሃ ጫካ ለጫካ እየተጓዘን አፋር ክልል ስንደርስ አባላ የሚባል አካባቢ የክልሉ ህዝብ ተቀብሎን ወደ መስመር አወጣን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የህወሓት ጽንፈኛ ቡድኑ በእኛ በፌደራል ፖሊስ አባላትና በሀገር መከላከያ ሰራዊት የፈጸመው አረመናዊ ድርጊት በጣም አሳዝኖናል፣በተለይ ከ10 ዓመታት በላይ አብሮን የሰሩና የኖሩ የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት ወደ ክልሉ ልዩ ሀይል በመቀላቀል አፈሙዝ ወደ እኛ በማዞር የፈጸሙብን ክህደት በጣም አሳዝኖናል፣ አስከፍቶናልም ብለዋል፡፡ 

ከዚህ ቀደም አባት አርበኞች ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለው ኢትዮጵያን እንዳስረከቡን ሁሉ ዛሬም በርካታ የሀገር ተቆርቃሪ የሆኑ ጓዶች ስላሉን ሀገራችን ለማዳን እየተከናወኑ ያሉ የህግ ማስከበር ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ እስከ መጨረሻ ከህዝብ ጋር በመቆም ለዚህ አስነዋሪ ድርጊት የተሰለፉትን የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ለህግ ለማቅረብ ለሚደረገው ርብርብ ኃላፍነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

 ሌላኛዉ የሰሜን ዲቪዥን፣ሶስት፣ሻለቃ 4፣ሻምበል 1 አባል ኮንስታብል ድረስ ንጉሴ እኛ ሰላም ነው ብለን በተቀመጥንበትና ባላሰብነው ሰዓት የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ተደራጅተው በመምጣት አንድ ዳቦ ለሁለት በመካፈል አብረውን ሲበሉ ከነበሩ ከትግራይ ተወላጅ የስራ ባልደረቦቻችን ጋር በመሆን ጥቃት ቢፈጽሙብንም የአፋር ህዝብ ላደረገልን አቀባበልና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

እኛ የትግራይ ህዝብን ከወንጀል በመከላከልና በክልሉ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ማህበራዊ እንቅስቃሴ ስናግዝና ስንተባበር ነው የቆየነው፣የትግራይ ህዝብ ይህንን ጽንፈኛ ቡድን በማጋለጥ ነጻነቱን ሊያረጋግጥ ይገባልም ብሏል፡፡(የፌ/ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top