Connect with us

ለአዛውንቶች ህልውና ሲባል ታዳጊ ልጆችን ጠመንጃ ማስያዝ ወንጀል ነው 

ለአዛውንቶች ህልውና ሲባል ታዳጊ ልጆችን ጠመንጃ ማስያዝ ወንጀል ነው – ሌተናል ጄኔራል ዮሐንስ ገ/መስቀል
Ethiopian press agency

ነፃ ሃሳብ

ለአዛውንቶች ህልውና ሲባል ታዳጊ ልጆችን ጠመንጃ ማስያዝ ወንጀል ነው 

ለአዛውንቶች ህልውና ሲባል ታዳጊ ልጆችን ጠመንጃ ማስያዝ ወንጀል ነው 

   – ሌተናል ጄኔራል ዮሐንስ ገ/መስቀል

 

ለ70 እና 80 ዓመት አዛውንቶች ህልውና ሲባል የእነርሱ የልጅ ልጅ የሆኑ የ17፣ 16 እና 15 ዓመት ልጆች አሰልጥኖ ጠመንጃ ማስያዝ ከሞራል አኳያ ነውር፤ ከህግ አንጻር ወንጀል መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ዮሐንስ ገ/መስቀል አስታወቁ ፡፡

ሌተናል ጄኔራል ዮሐንስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ግጭት የሚፈልግ ህዝብ አይደለም፡፡ በወንጀለኛ ቡድኑ በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የተፈጸመ ጥቃት በህዝቡም ላይ የተፈመው ወንጀል ነው፡፡

ይህ ቡድን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን መሳሪያ አስይዞ ለህልውናው ሲል በቀሰቀሰው ግጭት እየማገደ እንደሚገኝ ያመለከቱት ሌተናል ጄኔራል ዮሐንስ ፣ እነዚህ ሕፃናት መማርና ሰልጥነው ሥራ መያዝ ሲገባቸው ለዚህ ቡድን አዛውንቶች ህልውና ማቆያ መስዋዕት ሊሆኑ እንደማይገባ አመልክተዋል፡፡

 “የትግራይ ህዝብ ከጦርነት ወደ ጦርነት እየተንከባለለ ህይወቱን እየገበረ የመጣ ህዝብ ነው። ከጠመንጃ ጋር ጎን ለጎን የሚኖር ህዝብ ነው። ከዚህ መገላገል አልቻለም። ከብዙ መስዋእትነት በኋላ ዛሬም እነዚያው ሰዎች አፍነው እንዲሰቃይ እያደረጉት ናቸው። ለዚህ ደግሞ በልዩ ኃይሉ ውስጥ የተካተተው ወጣት ከዕድሜ በታች የሆነና ፣ለውትድርና የሚበቃ አለመሆኑ የዚሁ እውነታ ማሳያ ነው “ብለዋል።

ሰዎቹ ከአዲስ አባባ ሸሽተው እንደሄዱ ያሰቡት ስለ ትምህርት ወይም ስለ ሙያ ሳይሆን፤ ህዝቡን አጭበርብረው ገብተው ይሄንን መንግሥትና አገሪቱን በማብጠልጠን ህዝቡ እነሱን እንዲከተል ማድረግ ነበር ያሉት ጀነራሉ ፣ያ ካልሆነ ደግሞ አገሪቱን እናበጣብጣታለን የሚል ነበር። የዚህ ሁሉ ምክንያታቸው ደግሞ እንዳንነካ በሚል ስጋት ነው። ይህ ደግሞ ድንቁርናም ፤ ፍርሐትም ፤ ወንጀልም እንደሆነ አስታውቀዋል።(ኢኘድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top