Connect with us

የህወሓትን የሽብር ተግባር የሚቃወሙ ሰልፎች በሲዳማና በኦሮምያ እየተካሄዱ ነው

የህወሓትን የሽብር ተግባር የሚቃወሙ ሰልፎች በሲዳማና በኦሮምያ እየተካሄዱ ነው
Photo: Social media

ዜና

የህወሓትን የሽብር ተግባር የሚቃወሙ ሰልፎች በሲዳማና በኦሮምያ እየተካሄዱ ነው

የህወሓትን የሽብር ተግባር የሚቃወሙ ሰልፎች በሲዳማና በኦሮምያ እየተካሄዱ ነው

~ በአዲስአበባ መከላከያ ሰራዊቱን ለመደገፍ የደም ልገሳ ተጀምሯል፣

 

 የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው

 የህወሃት ቡድን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል  በጅማ እና አጋሮ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ ቡድኑ በሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊት በቡድኑ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር ዘመቻ የሚደግፍ ነው።

በሌላ ዜና የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን!”በሚል የደም ልገሳ በማካሄድ ላይ ናቸው ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት የጥፋት እና ክህደት የፈጸመብንን የህውኃት ቡድንን  በመፋለም የኢትዮጵያችን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ውድ ህይወቱን መስዋዕትነት  በመክፈል ላይ ላለው መከላከያ ሰራዊታችን ደማችነን በመለገስ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት አለብን ብለዋል ።

በህወሃት ጁንታ ወንጀለኛ ቡድን አመራሮች ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻን በድል እየተወጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚልሻ አባላት የላቀ ድጋፍ እና ክብር መስጠት ይገባል ብለዋል ።

በዘመቻው ተሳትፎ በማድረግ ላይ የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ሃይል እና የሚልሻ አባላት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል ።

ህብረተሰቡም በየአካባቢው በተዘጋጁ የድጋፍ ማእከላት በመነኘት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚችለውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ወ/ሮ አዳነች ጥሪ አቅርበዋል ።

“ከመከላከያ  ሃይላችን ጎን እንቆማለን!፣

ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን!እና

ደማችን ለክንደ ብርቱው ሠራዊታችን!በሚሉ መሪ ቃሎች  የአዲስ አበባ አስተዳደር አመራሮች፣ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሁሉም ክፍለከተሞች ደም በመለገስ ላይ ይገኛሉ ።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top