Connect with us

በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ እናወግዛለን

በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ እናወግዛለን
Photo: Social media

ዜና

በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ እናወግዛለን

በምዕራብ ኦሮሚያ የተፈጸመውን ግድያ በጽኑ እናወግዛለን

~ “ኦነግ – ሸኔ በሚባል ስም ራሱን የሚጠራ ድርጅት አላገኘንም” 

(የኦነግ መግለጫ –ህዳር 3, 2020ዓም)

 

ከትላንት በስትያ (እኤአ) ህዳር 1, 2020ዓ.ም በምዕራብ ኦሮሚያ በዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ከመገናኛ ብዙሃን የሰማን ሲሆን፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይህንን የግድያ ተግባር በጽኑ እያወገዘ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘንም ይገልጻል።

መንግስት ነኝ የሚለው ኣካል ካሁን ቀደም እንደለመደው ይህንን ግድያ የፈጸሙት ህወሃትና ኦነግ-ሸኔ ናቸው በሚል ገልጿል። ኦነግ-ሸኔ በሚል የሚታወቅም ይሁን በዚህ ስም እራሱን የሚጠራ ድርጅት ግን ኣላገኘንም። ለኢትዮጵያ ህዝቦችም ይሁን ለዓለም ማህበረሰብ በዚህ ስም የሚከሰሰው ድርጅት ማንነት ግልጽ ኣይደለም። 

ይህ የግድያ ድርጊትና ሌሎች መሰል ድርጊቶች ሁሉም ነጻና ተዓማኒነት ባለው ገለልተኛ ኣካል በኣጭር ጊዜ ውስጥ ተጣርተው ለተጎጂዎችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲሁም ለዓለም ማህበረሰብ ግልጽ እንዲሆኑ እንጠይቃለን። ከዚህ ባሻገር ሁሉም ኣካላት ህዝቦችን የሚያጋጩና በብሄሮች መካከል መጠራጠርን የሚፈጥሩ ማናቸውንም ዓይነት መረጃ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም ዜጎችን ለከፋ ኣደጋ እያጋለጠ ያለው ቀውስና የደህንነት ችግር ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት መፍትሄ ካልተበጀለት ይበልጥ እየተባባሰ እንደሚሄድ ኦነግ በመግለጫው ሲያሳስብ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፡ ኣሁን እያየን ያለነውን ኣደጋ ለማስቀረትና ኦሮሚያና ዜጎችን ለከባሰ ቀውስ ለመታደግ ያለው ብቸኛው መፍትሄ የኦሮሚያ ሽግግር መንግስት ማቋቋም በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያችንን በድጋሚ እናድሳለን።

በድጋሚ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በምዕራብ ኦሮሚያ በዜጎች ላይ የተፈጸመውንና ካሁን ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ የተፈጸሙ ግድያዎችን ሁሉ በጥቅብ እንደሚያወግዝ እያሳሰበ፡ ለሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች እንዲሁም ሰላም ወዳዶች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ህዳር 3, 2020ዓም

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top