Connect with us

ተቀባይ ያገኘው የአንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ጥሪ፤

ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ተቀባይ ያገኘው የአንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ጥሪ፤

ተቀባይ ያገኘው የአንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ጥሪ፤
ከዓለም አደባባይ እስከ ሀገር ቤት በአንድ ልብ፤

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬቲዩብ)
ለዚህ ነበር ያልተመቸናቸው፡፡ ብዙ ልቦች ስንመስላቸው ከአንድ ልብ በላይ አንድ ሆነን ተመለከቱ፡፡ ደካሞች ሆነን በሀሳባቸው በፊታቸው በጥንካሬ ቆመን ታየን፡፡ በዓለም አደባባዮች ከቁጥራችን በላይ በቃ የሚለው ከዳር ዳር ተሰማ፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትልውደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጎን ቆመው ሌላ የህልውና ዘመቻ ዘመቱ፡፡ በኢትዮጵያ ተራሮች ሳይሆን በዓለም ጎዳናዎች፡፡ ደግሞ ኪሳቸውን ለመፈተሸ አልሰሰቱም፡፡ መከራውን እንዲህ እያለፍነው ነው፡፡ ደስታውን አብረን እንስቀዋለን፡፡

አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ይመጣ ዘንድ ጥሪው ቀረበ፡፡ አሁንም እንደ አውደ ውጊያው፣ እንደ ዲፕሎማሲው፣ ሁሉ በዚህ ጥሪ ጉዳይ የሀገር ልጅ በአንድ ልብ አብሮ ቆመ፡፡ ከአየር መንገድ እስከ ኢምባሲ፣ ከዲያስፖራ ተግባር ምክር ቤት እስከ ዲያስፖራ ማኅበር፡፡

ሀገሩን የናፈቀ በአሰቴር አወቀ ሙዚቃ “እመጣለሁና ዘንድሮ ለገና” ብቻ ብሎ ቆዝሞ ላይቀር ጥሪውን ተቀበለ፡፡ የሰሞኑ መረጃዎች የልቦቻችንን አብረው መቆም አሳይተዋል፡፡ አየር መንገዱ እስከ ገና ያለው በራራ በጥሪው መሰረት ገና ታህሳስ ባዕታ ከመሆኑ በፊት ሞላ፡፡

ጥሪውን ተከትሎ የአፍሪካ ምልክት የሆነው አየር መንገዳችን የአየር ትኬት ዋጋ ቅናሽ አደረገ፡፡ ወዲያው ቁጭ ብለው የመከሩት የሆቴል ዘርፍ ባለድርሻዎች ቤታችን የወገን ነው ብለው ቅናሻቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ የመኪናው ኪራይ፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ የአካባቢ አስጎብኚዎች ሁሉም እንግዳ ተቀባይ ነን አሉ፡፡ ከሩብ የበለጠ ቅናሽ ከዳር ዳር ተሰማ፡፡

በመንግስት በኩል እነኛን በዓለም አደባባይ #NO MORE ያሉ ኢትዮጵያውያን የታደሰም ይሁን ግዜው ያለፈበትን መታወቂያ /Ethiopian origin ID/ ይዘው በልዩ ሁኔታ በትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸው ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደሚችሉ የገለጸው ብዙዎችን አነቃቃ፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም በኮቪድ፣ ቀጥሎም በሰሜን ኢትዮጵያ በተነሳ ወራሪ ጥፋት የጨለማ ዘመን እያሳለፈ ነው፡፡ ብዙ መከራዎችን፣ ዓለም አቀፍ ጫናዎችንና፣ ሴራዎችን በተባበረ ክንድ በምንመክትበት በዚህ ወቅት አበቃለት የተባለውን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግም ካጎነበሰበት ቀና ለማድረግ የአንድ ሚሊዮን ዲያስፖራ ጥሪ ሌላ ተስፋ ሰንቋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት ለሚገቡት እና ጥሪ በተደረገበት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለሚመጡት የእኛ ሰዎች ኢሚግሬሽን እንደ ወዳጅ አየር መንገድ ጠብቆ የመዳረሻ ቪዛ /on arrival visa/ አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁሞ አስቀድሞ በኦንላይን ማመልከቱ ደግሞ ድካምን የሚቀንስና ጊዜን የሚቆጥብ እንደሆነ መክሯል፡፡ ለዚህም የተቋሙ ህጋዊ ድህረ ገጽ www.evisa.gov.et በሆነው መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

ይሄ አዲስ አብዮት እንዲህ እንዲህ እያለ በዓመት አምስት ጊዜ ወገንን ከየአለበት በመጥራት ዓለም ከኢትዮጵያ ፊቱን ቢያዞር እኛ ከፊቷ ከቆምን አንዳች ፈተና እንደማይጥላት ማሳያ ይሆናል፡፡ ከሚመጡት እንግዶች ከሚገኝ ገንዘብና የሥነ ልቦና ጥገና ባለፈ በዓለም ዘንድ ብዙ የተወራላት ሀገር በአንድ ወር እንዲህ ያለ ተጓዥ ከዓለም አስተናግዳ በድል ስትወጣ እንደማየት ልብ የሚሞላም ነገር የለም፡፡

ኢትዮጵያውያን አብረን ከቆምን፤ ዓለም አብሮን ለመቆም ይገደዳል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top