Connect with us

አርበኛ የምታከብር ከተማ እራሷ አርበኛ ናት፡፡

አርበኛ የምታከብር ከተማ እራሷ አርበኛ ናት፡፡
ሄኖክ ስዩም

ማህበራዊ

አርበኛ የምታከብር ከተማ እራሷ አርበኛ ናት፡፡

አርበኛ የምታከብር ከተማ እራሷ አርበኛ ናት፡፡

ስለ ፋኖ አጋየ ቤት ሽልማት-ጎንደር ሆይ እናመሰግንሻለን!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬቲዩብ)

አርበኛ እወዳለሁ፤ በተለይ እንደ አጋዬ ያለ፡፡ በፍቅር ሲመጡ ባሪያ፡፡ ለወደደው ፈሪ መሳይ፡፡ በሀገር ከመጡበት ደግሞ ብቻውን ታሪክ፡፡ እሱ ስሜን ነው፡፡ ግን ታሪክ ደግሟል፤ የገረሱ ዱኪን፣ የአያሌው ብሩን፣ የባልቻ ሳፎን፣ የገበየሁ ጎራውን፣ የአበበ አረጋይን ታሪክ ደግሟል፡፡

እነሱ ስሙን የሚነግዱበት አሉላ አባነጋ ለሀገሩ ሳይነጋ ከተፍ እሚል እንጂ በተንቤን አልያም በትግራይ ፍቅር የነደደ አልነበረም፡፡ አሉላን እመስላለሁ ካለም አጋዬ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ አጋዬ አድማሱ የሀገሬን ጀግኖች የሚመስል የዘመኔ ፋኖ፡፡

ዛሬ ደስ የሚል ዜና ሰማሁ፡፡ ጎንደር አርበኛውን አመሰገነችው፡፡ ለአጋዬ አድማስ ቤት መስጠት ማመስገን እንጂ መሸለም አይደለም፡፡ እሱ ሀገር ሊሰጥ ቤቱን ትቶ ሜዳ የወጣ ልበ ሙሉ ነው፡፡

ሁሌም ሀገራዊ ግዳጁን ሲጨርስ ጡሩኝ አልያም ሹሙኝ አይልም፡፡ ጀብድህን ተናገር ሲባል ሀፍረት የሚገድለው ድል አድራጊ ነው፡፡ አሁን ሀገር ለማዳን ክተት ጥሪውን ተቀብሎ ገብቷል፡፡ ሀገሩ ሰላም እንድትሆን እስከ ሞት ራሱን የሚሰጥና እንዲህ ይሁንልኝ ብሎ እጁን ለጠላትም ለኩርፊያም የማይሰጥ ኩሩ ነው፡፡

ጎንደር የአርበኛውን የፋኖ አጋየን ውለታ አስባለች፡፡ አመሰግናለሁ ያለችው ስጦታ ይዛ ነው፡፡ ሀገር በማዳኑ ዘመቻ በግንባር ከፍተኛ ተጋድሎ እየፈጸመ ለሚገኘው አርበኛ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ዞብል ክፍለ ከተማ መኖሪያ ቤት አበርክቶለታል፡፡

አርበኛዋ ከተማ የዞብል ክፍለ ከተማ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ለፋኖ አጋየ አድማስ ቤተሰቦች ዛሬ አስረክቧል። ጎንደር የራሷን አይደለም የሀገር ውለታ መልሳለች፡፡

እንደ ፋኖ አጋየ ያሉ ጀግኖች የደም እዳ ገና አጉብጦ ያኖረናል፡፡ በእውነተኛ ጀግኖች ባንዳና ሆዳሙ ባይሸነፍና ድል ባይነሳ በየዘመናቱ ክብሯ የታደሰ ሀገር ባልኖረችን ነበር፡፡

ዛሬ ቁልፉን የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አወቀ አስፈሬ ለአጋየ ቤተሰብ ማስረከባቸውን የከተማው ኮሙኒኬሽን ይፋ አድርጓል፡፡ በቁልፍ ርክክቡ ወቅትም አቶ አወቀ አሸባሪው እና ወራሪው ትህነግ በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ጦርነት መሰረት አድርጎ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በብርቱ እየተፋለሙት መሆኑን ጠቅሰው አርበኛ ፋኖ አጋየ አድማስም በግንባር ቀደምትነት ቤተሰቦች ትቶ በመዝመት ጠላትን እየተዋጋ ይገኛልና እሱን አለማበረታት እንደ ንፉግነት ይቆጠራል፡፡ ማለታቸውን የከተማው ኮሙኒኬሽን ገጽ ላይ ሳነብ ልቤ በደስታ ተሞላ፡፡

ለፋኖ አጋየ መኖሪያ ቤቱን ለመስጠት የወሰነው የዞብል ክፍለ ከተማ ሥራ አስፈጻሚ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ገብረሚካኤል አየልኝ መግለጻቸውን ከመረጃው አንብቤያለሁ፡፡

መቼም አጋየን ከመውለድ በላይ ሀብታምነት የለም፡፡ ደግሞ የእናቱ ስም ሀብታም ነው፡፡ እማማ ሀብታም መኮንን የአጋየ እናት ልጄ ለሀገር እየከፈለ ያለውን ዋጋ በሚገባ ተረድታችሁ ይህንን ስጦታ በማበርከታችሁ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

ጎንደር ከተማ ናት፡፡ የታሪክና የቅርስ ከተማ፤ ደግሞ አርበኛ ናት፡፡ አርበኛ ያከበረች ባለውለታ፡፡

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

 • ማህበራዊ

  የአጎዋ ጉዳይ!..

  By

  የአጎዋ ጉዳይ!.. (ሙሼ ሰሙ) የባይደን አስተዳደር ለኢትዮጵያ ተፈቅዶ የነበረውን የአጎዋ ከቀረጥ ነጻ ተጠቃሚነት ሰርዟል፡፡ እ.ኤ.አ በ2020...

 • ከቁዘማ መልስ ከቁዘማ መልስ

  ማህበራዊ

  ከቁዘማ መልስ

  By

  ከቁዘማ መልስ (ሙክታሮቪች ዑስማን) በሀገር ጉዳይ መረጃ ማቅረብ የመንግስት ግዴታ ነው። የዜጎች መብት ነው። በርግጥ የጦርነት...

 • በዋቤ ሸለቆ ከጉራጌ ደግ ልብ ጋር በዋቤ ሸለቆ ከጉራጌ ደግ ልብ ጋር

  ማህበራዊ

  በዋቤ ሸለቆ ከጉራጌ ደግ ልብ ጋር 

  By

  በዋቤ ሸለቆ ከጉራጌ ደግ ልብ ጋር  (ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ዋቤ ሸለቆ ወርዷል፡፡ የውሃ ቱሪዝም...

 • የጠ/ሚ ዐብይ አህመድ መልዕክት:- የጠ/ሚ ዐብይ አህመድ መልዕክት:-

  ማህበራዊ

  የጠ/ሚ ዐብይ አህመድ መልዕክት:-

  By

  የጠ/ሚ ዐብይ አህመድ መልዕክት:- እንኳን ለ1496 ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! መውሊድ አላህ በነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)...

 • በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና

  ማህበራዊ

  በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና

  By

  በኢትዮጵያ ፀሐይ ያጠላው ጥቁር ደመና (ፍትሕ መጽሔት ~ ቹቹ አለባቸው ) የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት ከ120 ዓመት...

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top