Connect with us

የአሜሪካኖች ነገር!.

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-
Social media

ነፃ ሃሳብ

የአሜሪካኖች ነገር!.

የአሜሪካኖች ነገር!.

(ሙሼ ሰሙ)

በአሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ ኋላፊነት የያዙ ፖለቲከኞች አጀንዳቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየሆነ ነው ። የሰብአዊ መብት ጥበቃና የእርዳታ እህል አቅርቦትን በማሳበብ የጀመሩት ክስ እየከረረ ወደ ሽግግር መንግስት ማቋቋም አድጓል ፡፡ የታላቋ አሜሪካ ፖለቲከኞች ለቅድመ ዝግጅት እንዲረዳቸው የፌዝ ስብሰቦችን “በኮንፌዴሬሽንና በፌዴሬሽን” የዳቦ ስም በማቀናጀት የወደፊት መሪዎቻችንን ከወዲሁ መርጠውልና፡፡

ትናንትም በተካሄደው የሴኩሪቴ ካውንስ ስብሰባ ላይ የአሜሪካንን መንግስት የወከሉት ሊንዳ ቶምሰን አዲስ አበባ ውስጥ ጦርነት ያለ በማስመሰል የዜጎቻችን ደህንነት ስለሚያሰጋን ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ ያለንን አቅም ልንጠቀመ እንችላለን ብለዋል፡፡

ልብ እንበል፣ በሰብአዊ መብትና በእርዳታ እህል አቅርቦት ሰበብ የተቀነባበረው ክስ በተባበሩት መንግስታትና በሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተጣርቶ መንግስት ለመገልበጥና አሻንጉሊት መንግስት ለማቋቋም የሚያበቃ ጭብጥ እንደሌለው ሲታወቅ፤ አዲስ ክስ ፈብረከው የዜጎቼን ደህንነት ለማስከበር ሲባል ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ እወስዳለሁ ወደሚል ቅደመ ጦርነት “ላሌ ጉማ” ተሿግሯል።

የአሜሪካ ውሳኔ ሰጭዎች የዜጎቻችንን ደኅንነት ማስጠበቅ በሚል ሰበብ ጦር በመሰብቅ፣ ሀገር በመውረር፣ መንግስት በመገልበጥና ሀገር በማፍረስ የተካኑ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም የተደቀነባት ፈተና ይህው ነው፡፡ ብልጽግና ኖረም አልኖረ፣ ጦርነቱ ቆመም አልቆመ ቁም ነገሩ እሱ አልሆነም፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከግብጽ ጀምሮ ለማንም ስጋት መሆን የማትችል በአሻንጉሊት የምትመራ ወይም ደካማ ትንንሽ ሀገር ማድረግ ላይ ቆርጠው እየሰሩ ነው፡፡ ለዋሽንግተን ፖለቲከኞች ምክንያት ከውጤት በኋላ የሚፈበረክ ተራ ጉዳይ ነው። የቤት ስራውን ደግሞ ለእኛው ሰጥተውናል።

ከታሪክ ምን እንማራለን። አሜሪካዊና እንግሊዛዊ የታሪክ ምሁር የሆኑት ክሪስቶፈር ኬሊና ሰቱዋርት ሌይኮክ “አሜሪካ ኢንቬድስ” በሚለው መጽሃፋቸው አሜሪካ በተመድ ከተመዝግቡ 193 ሃገራት መካከል 84ቱን እንደወረረች ዘግበዋል፡፡ ከነዚህ ሀገራት ውስጥ በመቶ ዘጠና አንዱ ሀገራት የውሰጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ጦርነት እንዲቀሰቀስ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በመቀስቀስና መንግስት በመገልበጥ ሕዝብንናና ሀገራትን ለመከራ ዳርገዋል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top