Connect with us

በዚህ ጦርነት እንደ አዳነች አበቤ ሀገሩን ለማዳን ቆርጦ የተነሳ አላየሁም፤

ነፃ ሃሳብ

በዚህ ጦርነት እንደ አዳነች አበቤ ሀገሩን ለማዳን ቆርጦ የተነሳ አላየሁም፤

በዚህ ጦርነት እንደ አዳነች አበቤ ሀገሩን ለማዳን ቆርጦ የተነሳ አላየሁም፤ አዳነች-እውነትም አዳነች!!

(ስናፍቅሽ አዲስ ~ድሬቲዩብ)
አዳነች አሁን የአዲስ አበባ ከንቲባ ብቻ አይደለችም፡፡ በአደባባዮች ቆማ የሀገርን ፍቅር፣ የኢትዮጵያን ህልውና የምትሰብክ የህዝባዊ ንቅናቄው መሪ ናት፡፡ ትህነግ ሀገር ከወረረችበት፣ የሀገር ዘብ ካረደችበት ጊዜ አንስቶ ዛሬ ድረስ ቃላቸውም ተግባራቸውም ሳይቀያየር አደባባይ ቆመው እውነትን ከተጋፈጡ መሪዎች የአዲስ አበባዋ ከንቲባ አዳነች አበቤ ዋናው ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ከሴት ባለስልጣናት አይደለም ከብዙ የወንድ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች ጭምር በበለጠ ሁኔታ የአዲስ አበባ ህዝብ በንቃት ጦርነቱን ባለቤት እንዲሆንበት ደጀንነቱን እንዲያሳይ ያለ እረፍት ሰርታለች፡፡

የከንቲባ ብዙ መድረኮች ሆይ ሆይ ናቸው አሁን የሚያስፈልገው ዘመቻ ነው የሚል ምንም ያልገባውና ባልገባው በመቀባጠሩ ሀገሩን እየጎዳ ያለው ጥቂት አካል ስለ ስንቅ፣ ስለ ዲፕሎማሲ፣ ስለ ጦርነት በጀት እውቀት የሌለው ነው፡፡

አዲስ አበባ በዚህ ወቅት ከፌዴራል መንግስቱ ቀጥሎ ለጦርነቱ ከፍተኛ በጀት በማቅረብ አለኝታነቷን ያሳየች ከተማ ናት፡፡ የዚህ መሀንዲሱም ሹፌሩም ከንቲባዋ ናቸው፡፡ ከዚያ ሲያልፍ የትህነግ ጀሌዎችን ስውር ደባና በከተማዋ የታሰበ ከባድ ወጥመድ ያለ ምንም ጉዳት በማክሸፍም በኩል ከንቲባ አዳነች እየሰሩት ያለው ስራ ሊመሰገን ይገባል፡፡

የጥቅምት ሃያ አራት ሀገር ክህደት ወንጀልን ተከትሎ በተከፈተው ህግ ማስከበር ዘመቻ የአማራ ክልል የገጠመውን የበጀት ቀውስ ቀድሞ በመረዳት መቶ ሚሊዮን ብር ይዘው ወደ ባህር ዳር ያቀኑ ሰው ናቸው፡፡

ከንቲባ አዳነች በብዙ የአዲስ አበባ መድረኮች ስለ ጁንታው ሀሳቡና ኢትዮጵያውያን ለምን ጦርነት እንደመረጡ በመግለጽ የተሻለ የምክንያት ሞጋችነታቸውን አሳይተዋል፡፡

አዳነች ሀገር በማዳኑ ተልእኮ ቅድሚያ የቆሙ፣ በጽኑ አቋም እና በወኔ የታዩ፣ በድንቅ አነቃቂ መልእክቶቻቸው ያስደመሙ፣ ነዋሪዎቻቸው ደጀን ይሆኑ ዘንድ ብዙ ቢሊዮን ብሮች ለሀገር መከላከያ እንዲደርስ ያደረጉ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና አለን በማለት ደጋግመው አስገራሚ ነገር ያደረጉ መሪ ናቸው፡፡

አገዋን የአድዋ ልጆች አንበረከክበትም ብለው አቋማቸውን ያጸኑ፣ የመዲናዋ የኢኮኖሚ አሻጥር እየታገሉ፣ የአዲስ አበባን ህዝብ ደጀን አድርገው እያታገሉ፣ ከባህር ዳር ፖለቲከኞች ቀድመው አመራሮቻቸውን ግንባር በማሰለፍ አርአያ የሆኑ ሰው ናቸው፡፡

ሰው በሰራው መልካም ስራ ካልተመሰገነ ክፉ ሰሪው ገኖ ይኖራል፡፡ እዚህ ጋር ሌላ ዓላማ ያለው ወይም ያላወቀ ሰሞኑን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲንሸራሸር የከረመውን የወሎ ተፈናቃይ አዲስ አበባ እንዳይገባ አደረጉ የሚል ትችት ባያነሳ እመርጣለሁ፤ ምክንያቱም ይሄንን አላደረጉም፤ ይሄ እየሸሸ ቀዬውን ለቆ የሚሮጠው ሰው በስውር የተሰገሰገ ሀገር አጥፊ ጉያው አቅፎ ደሴ ቢገባ የሆነውን ሀገር አይቷል፡፡ ይሄ ውሳኔ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን መርጦ ለማርያን አልፎ ባህር ዳርም እንዳይገባ መደረጉን ጸሐይ የሞቀው ነው፡፡ ሌላ ፖለቲካ ትርጉም መስጠት አእምሮ ያቆሽሻል እንጂ መፍትሔ አይደለም፡፡

ይልቁንም የአዲስ አበቤዋ ከንቲባ አዲስ አበቤን አንቅተው እና አሳትፈው አሁንም ሀገር የማዳኑን ዘመቻ ከፊት ቆመው ከሚመሩት አንዷ ሆነዋልና እኛ አዲስ አበቤዎች ኮርተንባቸዋል፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top